የአዊ ብሔ/አስ/ ህገ-መንግስቱ ያጐናፀፈውን መብት ተጠቅሞ ከ1987 ዓ/ም ወዲህ አንድ የብሔረሰብ አስተዳደር ሆኖ ተቋቁሟል፡፡ ብሔ/አስተዳዳሩ በአማራ ክልል ደቡባዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን በክልላችን ከሚገኙ ሶስት የብሔሰብ ዞኖች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ቀድሞ ከሶበር በመባል ትታወቅ የነበረችው የብሔረሰብ አስተዳደሩ ርዕሰ ከተማ ከቅርብ አመታት ወዲህ እንጅባራ በመባል ትጠራለች፡፡ ከአዲስ አበባ ባህርዳር በደብረ ማርቆስ መስመር በ450 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ የአብዛኛው የብሔረሰቡ ህዝብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ አዊኛ ይሁን እንጅ አማርኛም በስፋት ይነገራል፡፡ ጉምዝኛም በዞኑ በጥቂቱ ከሚነገሩ ቋንቋዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ብሔረሰብ አስተዳደሩ በሰሜን ጐንደር፣ በምስራቅ እና በደቡብ ምስራቅ ምዕራብ ጐጃም፣ በምዕራብ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ በደቡብ ኦሮሚያ ክልል የሚያዋስኑት ሲሆን አስተዳደራዊ መዋቅሩም በስምንት የገጠር ወረዳዎች እና በሶስት የከተማ አስተዳደሮች የተደራጀ ነው፡፡
ከ1 ሚሊዮን 78ሽ 235 ህዝብ ያለው አዊ ብሔረሰብ የቆዳ ስፋቱ 857ሽ 886 ሄ/ር ሲሆን ተፈጥሯዊ አቀማመጡን ስንመለከት በአብዛኛው ሜዳማ አልፎ አልፎ ወጣገባ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ከ700-2920 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ያላቸው ቦታዎችም ይገኛሉ፡፡ የአየር ንብረቱ 17 ከመቶ ደጋ፣ 72 በመቶ ወይና ደጋና 11 ከመቶ ቆላማ ነው፡፡ በዞኑ በገጠር 929ሽ 858 ህዝብ የሚኖር ሲሆን ቀሪው 14 8ሽ 377 ህዝብ በከተማ ይኖራል፡፡8 የገጠር ወረዳዎችና 3 የከተማ አስተዳደሮች አሉት፡፡
ብሔረሰብ አስተዳደሩ ከዛሬ 20 ዓመት በተለይም ራሱን በራሱ ማስተዳደር ከጀመረበት ከ1987 ዓ/ም ወዲህ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ፣ምቹ የተፈጥሮ ሀብትና ታታሪ ህዝብ ባለቤት ነው፡፡

No comments:
Post a Comment