Wednesday, 19 April 2017











ውድ የዙራሙሪ መፀሔታችን አንባቢዎቻችን በዚህ እትማችን በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር  ተወላጅ የሆነው ለረጅም ዓመታት በወጌሻ ሙያተነኝነት እና በመምህርነት ለህ/ሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኘው ብርቅየ   አቶ አያና   ታረቀኝን ይዘንላችሁ ቀርበናል መልካም ንባብ
· ዙራሙሪ- የተወለድክበት እና ያደግህበት ቦታ ?
· አቶ አያና-- በአዊ ብሄ/አስ/በፋግታ ለኮማ ወረዳ አስዋ ፊንዚት ቀበሌ ነው፡፡
· ዙራሙሪ-- የትምህርት ደረጃ ?
· አቶ አያና-- 12+4  (ቋንቋ) ድግሪ
· ዙራሙሪ-- መደበኛ ሥራህ አሁን ላይ?
· አቶ አያና-- በአዲስ ቅዳም ከተማ በጉልህ አጠ 1 ደረጃ /ቤት በማስተማር ላይ እገኛለሁ፡፡
· ዙራሙሪ-- ለስንት ያህል ዓመታት በመምህርነት ሙያ ላይ ትገኛለን?
· አቶ አያና-- 13 ዓመታት በማስተማር ላይ እገኛለሁ፡፡
· ዙራሙሪ-- የወጌሻነት ሙያ እንዴት ተማርከው?
· አቶ አያና-- 1979 12 ክፍል ትምህርቴን ካጠናቀቅኩ በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ባለማምጣቴ ወደ ግብርና ህይወት ገባሁ፡፡
· 14 ዓመታት በተወለድኩበት አካባቢ ትዳር መስርቼ ግብርናን መተዳደሪያ አደረግሁት፡፡ በግሌ በዚህ ዓመታትም የወጌሽነት ሙያውን ከአባቴ የወረስኩት በመሆኔ ለአካባቢው ማህበረሰብ አገለግል ነበር፡፡



አቶ አያና በወጌሻ ሥራ ላይ/በአዲስ ቅዳም/  
· ዙራሙሪ-- ስለ አባትህ ትንሽ አውራኝ?
· አቶ አያና--  አባቴ በጣም የታወቀ የወጌሻ ባለሙያ ነበረ፡፡
ሠውንም ከብትንም በቀላሉ የሚያጥን፣በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ያገለግል ነበር፡፡ በዚያን ወቅት አባቴን በምረዳበት ጊዜ ሙያውን መውረስ ችያለሁ፡፡ ስለሆነም ሙያው የአባቴ ውርስ ነው፡፡
· ዙራሙሪ-- እንዴት ወደ መምህርነት ሙያስ ገባህ?
· አቶ አያና-- 1994 / በግሌ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በድፕሎማ መረሃ ግብር መማር ጀመርኩኝ፤ትምህርቴን ካጠናቀቅሁ በኋላም እስከ 1997 / በቋሪት አካባቢ ማስተማር እና የወጌሻ ስራየንም ጎን ለጎን እሰራ ነበር፡፡


· ዙራሙሪ-- እንዴትስ ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ መግባት ቻልህ?
· አቶ አያና-- 1998 . በዝውውር የመጣሁ ሲሆን ራቅ ያለ ቦታ  ተመድቤ በማስተምርበት ወቅት አዲስ ቅዳም በመመላለስ ሠዎችን የማጠን አገልግሎት ስሰራ ቆይቻለሁ፡፡ ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ ለመግባቴ ምክንያት (የረዱኝ) የአዲስ ቅዳም ከተማ /ሰብ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው ጥያቄ በማቅባረባቸው  ከተማ ገብቼ እንዳስተምር ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል፡፡
ለወጌሻ ስራ የሚጠቀማቸው መደሃኒቶች እና ቁሳቁሶች
·  ዙራሙሪ-- ማስተማርና የወጌሻ ስራውን እንዴት አጣጥመህ እየሰራህ ነው ?
· አቶ አያና-- በተለይም ካለፉት 8 ዓመታት ወዲህ ከማታው 800 ሰዓት በፊት ተኝቼ አላውቅም፡፡ ቀን ግማሽ ሽፍት አስተምራለሁ፡፡ ከዚያ በኃላ እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት የወጌሻ ስራየን እሰራለሁ፡፡
ለተማሪዎቼም ምንም አይነት የሠዓት መሸራረፍ ሳይታይብኝ ያለኝን እውቀት ለማስተላለፍ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ የተሻለ እውቀት እንዲኖረኝም ዲፕሎማ በባይሎጅ፣ድግሪ ደግሞ በቋንቋ በራሴ ጥረት ተምሬያለሁ፡፡
· ዙራሙሪ-- ለምን ያህል ዓመታት ባህላዊ ወጌሻ ሙያውን እየሰራህ ትገኛለህ ?
·  አቶ አያና-- 27 ዓመታት
·  ዙራሙሪ-- የባህላዊ ወጌሻ አይነቶች ምን ምን ናቸው ?

·  አያና-- የአጥንት ስብራት.ውልቃት፣ወለምታ፣የሥር መዞር፣የነርብ መደራረብ፣የጡንቻ መሸማቀቅ፣የላሉ ጡንቻዎችን እንዲጠነክሩ ማስተካከል፣እብጠት በተለየ መልኩ ማስወገድ ወደ ካንሰርነት እንዳይቀየር ማስቀረት፤አጠቃላይ የመገጣጠሚያ ችግሮች ያሉትን ሁሉ መፍትሔ የመስጠት ስራ እሰራለሁ እንዲሁም የመኪና አደጋ፣ደብደባ፣በጥይት መመታት፣እንዲሁም ከጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰቱ ለምሳሌ ዛፍ ላይ መውደቅ፣ፈርሶ ጉልህ፣መጠጥ እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
·  ዙራሙሪ-- በምን አይነት የዕድሜ  ክልሎች ያሉ የህ/ሰቡ ክፍሎችን ነው አገልግሎት የምትሰጠው ?
·  አቶ አያና-- ከህፃናት እስከ አዋቂ /6 ወር እስከ 80/ዓመታት ያሉ ሁሉ አገልግሎቱ ያገኛሉ፡፡
·  ዙራሙሪ-- እንዴት አይነት እርዳታ ቢደረግላቸው ከጉዳታቸው መዳን ይችላል ?
·  አቶ አያና-- ማንኛውም ጉዳት የቅርብ ክትትል ቢደረግለት ፍቱን ምላሽ (ወዲያው ከበሽታው የመዳን) ባህሪ ያጋጥማቸዋል፡፡ክትትሉን ሌትም ቀንም ተግተው ከወሰዱ  በቀላሉ መዳን ይችላሉ፡፡
· ዙራሙሪ-- አሁን ከብሄረሰብ አስተዳደራችን በተጨማሪ በሌሎች  አከባቢዎችም ታዋቂ እየሆንክ መጥተሃል በአንድ ሠው አገልግሎቱ መስጠት አይከብድም ?
· አቶ አያና-- ከክልላችን አልፎ በሀገሪቱ ባሉ ሌሎች ክልሎች እስከ ሱዳን ድረስ በመምጣት አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል፡፡
ተኝቶ ክትትል የሚደረግለት እና አዲስ 50 በላይ ሰዎች በቀን  እርዳታ ይደረግላቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ከመንግስት ስራ ጎን ለጎን በትርፍ ሰዓት ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት ነው
· ዙራሙሪ-- የምትጠቀማቸው የወጌሻ መደሃኒቶች ምንድን ናቸው ?
· አቶአያና--ባዝሊን፣ሚንዛ፣ቤታ ሳሊሳይሴት፣የወይራ ዘይት፣የጥቁር አዝሙድ ዘይትና ሌሎችን እጠቀማለሁ፡፡

ደምቶ ለሚመጣው ጓንት እጠቀማለሁ፡፡
· ዙራመሪ-- ገጠር ላይ 14 ዓመታት የወጌሻነት ስራህን ስትሰራ የምትጠቀማቸው ግብዓቶች ?
· አቶ አያና-- ባዝሊን፣ቅቤና የበግ ቅልጥም (መቁን) ብቻ ናቸው፡፡
· ዙራሙሪ-- መማርህ (የመምህርነት ሙያህ) ለወጌሻ ስራህ ምን አስተዋጽኦ አድርጓል?
· አቶ አያና-- ከዚህ በፊት ገጠር ላይ በምሰራበት ጊዜ በልምድ ብቻ እና የምጠቀማቸው ቅባቶች ውስን ነበሩ፡፡
አሁን ላይ ግን የአጥንት ክፍሎችን ማወቅ፣የተለያዩ አጋዥ መጸሐፎችንና በኢንተርኔት የሚላቀቁ ህክምናዎችን በመጠቀም ሙያውን እንዳሳድገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቶልናል፡፡
በአጠቃላይ የአጥንት ክፍሎችን፣የነርብ፣የጅማት እና ሌሎችንም ክፍሎችን ማወቅ እና ውጤታማ የወጌሻ ስራ እንድንሰራ አግዞኛል፡፡ ባህላዊ እና ዘመናዊ የወጌሻ አገልግሎት እንድሰራ ረድቶኛል፤ እንዲሁም ራጅ በማንበብ ህክምናውን የተሻለ እያደረግሁ ነው፡፡
· ዙራሙሪ--አገልግሎት መስጫ ቦታህ ምን ይመስላል ?
· አቶ አያና-- የምሰራበት ቦታ በመኖሪያ አካባቢ ሲሆን ወደ 48 የተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች አሉኝ፡፡
በተኝቶ መታከሚያ ቦታ እርዳታ ሲያደርግ
ዋጋቸውን 1 ቀን  10 ብር ነው፡፡ ግቢውም የውሃ፣የመጸዳጃ ቤት፣የማብሰያ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ይሠጣል፡፡







ወደዚህ አይነት አገልግሎት ለመስጠትም ያነሳሳኝ ተሰብረው የሚመጡ ሠዎች መሬት ላይ ሁነው ሲታከሙ ሊዛባ ይችላል፡፡ በአልጋ ላይ በሚሆኑበት ወቅት ግን ለክትትልና ቶሎ እንዲድኑ እገዛ ያደርጋል፡፡
·  ዙራሙሪ-- ክፍያውስ ምን ይመስላል ?
·  አቶአያና--ለረጅምወራት የሚቆይ፣ለሳምንት፣በቀናት (እንደየቀጉዳታቸው)የተመጣጠ ክፍያ አስከፍላቸዋለሁ፡፡
50-300 ብር ባለው የምጠቀማቸውን መደሃኒቶችን ግምት ውስጥ ያሰገባ ክፍያ አለው፡፡
· ዙራሙሪ-- በሙያህ /ሰቡን በምታገለግልበት ወቅት የመጀመሪያ እርካታህ ምንድን ነው ?
· አቶ አያና-- ሠዎች ከነበራቸው ስቃይ ማልቀቅ፣የዜያን ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ውስጣዊ እርካታ ይሠጠናል፡፡
· ዙራሙሪ-- ከመንግስት የተደረገልህ ድጋፍ እና እውቅና ምን ይመስላል ?
አቶ አያና-- የወጌሻ ስራውን ጎን ለጎን ለመስራት ያመቸኝ ዘንድ መንግስት ከገጠር ወደ ከተማ ገብቼ እንዳስተምር እገዛ አድርጎልኛል፡፡
· በሌላ በኩል የተሰጠኝ እውቅና ግን የለም፡፡ ምክንያቱም ጤና ጥበቃ ተደራጅ በሚሉኝ ወቅት እኔ የምደራጀው ሌላ ወጌሻ ባለመኖሩ አልተደራጀሁም
· ዙራሙሪ--  ማህበራዊና፣ቤተሰባዊ ኑሮህ ጋር የስራ መደራረብ ተፅዕኖ አላሳደረብህም?
· አቶ አያና-- በጣም ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ አሳድሮብኛል፡፡ 8 ዓመታት ወዲህ ሆቴል ተዝናንቼ ላውቅም፡፡
ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አልሳተፍም፤ከቤተሰቦቼ ጋር በአግባቡ አልገናኝም፡፡
· ዙራሙሪ-- ህብረተሰቡ እንዴት ነው አገልግሎቱን የሚያገኘው የወረፋው ጉዳይ ?
· አቶ አያና-- ለማስተላለፍ ለልጆቼ ዕቅዱ አለኝ፤የእኔ ሙያ የተከተለ እስከ አሁን የለም፡፡ ለወደፊቱ ለልጆቼ ለማስተላለፍ ዕቅድ አለኝ፡፡





· ዙራሙሪ-- ስንት ልጆች አሉህ ?
· አቶ አያና-- 4 ወንዶችእና 2 ሴት ዩኒቨርስቲ ድረስ በመማር ላይ ይገኛሉ፡፡
· ዙራሙሪ-- ቤተሰቦችህ ለሙያህ እያገዙህ ያሉት ?
· አቶ አያና-- በተለይ ባለቤቴ ለሙያው እገዛ ታደርግልኛለች፡፡ የእኔን የሥራ ጫና በማቅለል ጥረት ታደርጋለች፡፡
· ዙራሙሪ-- የባህላዊ የወጌሻ ሥራህ እንዲጎለብት ምን መደረግ አለበት ትላለህ ?
· አቶ አያና-- (ከዘመናዊ ህክምና) ጋር በጋራ ቢሰራ ሙያው ይሻሻላል፡፡ ጎን ለጎንም ባህላዊ ወጌሻ ለዘመናዊ ህክምና የራሱን የሆነ በጎ ተፅኖ አለው፡፡
· ዙራሙሪ-- የወደፊቱ የወጌሻ ሙያህ ዕቅድ ምንድን ነው /ራዕይህ/ ?አቶ አያና-- ሙያውን ለማሳደግ የመስሪያ ቦታየን በማስፋፋት ድሃውን /ሰብ ያመጣጠነ ክፍያ የሚከፍልበት ትልቅ የዘመናዊ ባህላዊ ወጌሻ ማዕከል መክፈት
· ዙራሙሪ ስለነበረን ቆይታ በዙራሙሪ ምጽሄታችን ስም እናመሰገናለን ?
· አቶ አያና እኔም አመሰገናለሁ
ይህ ብርቅየ የብሔ/አስተዳደራችን ተወላጅ፣መምህርና የወጌሻ ባለሙያ እየሰጠ ያለው መልካም አገልግሎት ለብሔ/አስተዳደራችን ገጽታ ግንባታ የራሱ የሆነ ታሪካዊ አሻራ እያኖረ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የሚመለከተው ሁሉ የመስሪያ ቦታ በመስጠት፣አቅሙን በማጎልበት፣ቁሳቁሶችን በመርዳት እንዲሁም በሚያስተምርበት አካባቢ ምቹ የመማር ማስተማር ጊዚያትን በማመቻቸት እገዛ ማድረግ ይጠበቃል ፤እኛም በአካል በመገኘት የሥራ እና የመኖሪያ አካባቢያውን የጎበኘነ ሲሆን ለሥራ ምቹ አለመሆኑን ተገንዝበናል፡፡


አቶ አያና ግን ሰለችኝ ደከመኝ ሳይል /ሰቡንና ተማሪዎቹን ባለው ሙያ በቅንነት እያገለገለ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ይህ ታላቅ ባለራዕይ ባለሙያን ማገዝ የሁላችንም የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል፡፡ መልካሙን ሁሉ ለአቶ አያና እና ቤተሰቦቹ ተመኝተናል አበቃን፡፡



No comments:

Post a Comment