Monday, 24 April 2017

 ሠላምና ልማት
አንድን ሀገር ወደ እድገትና ብልፅግና እንዲጓዝ የሚረዱት በተቃራኒው ደግሞ ኋላቀር ሆኖ እንዲኖር የሚያደርጉት ምክንያቶች አያሌ ቢሆኑም መሰረታዊ ከሚባሉት የኋላቀርነት ምክንያቶች መካከል ዜጎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወንጀል መፈፀም አንዱና ዋነኛ ነው፡፡ ማረሚያ ቤቶች በፍ/ቤት ትዕዛዝ ወደ ማረሚያ ቤት የሚላኩ ፍርደኛ፣ የቀጠሮ የህግ ታራሚዎችን ተቀብሎ ተገቢ ለውጥ እንዲያመጡ የጥበቃ፣ የእርምት፣ የሙያ ክህሎት፣ የስልጠና አገልግሎቶችን በማቅረብ ታርመውና ታንፀው እንዲወጡ በማድረግ ሠላማዊና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ነው፡፡ በዚህ መሰረት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶችም  የግንባር ቀደምትነት ሚናን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ውድ አንባቢያን በዚህ አምድ የአዊ ብሔ/አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች 2009 በጀት ዓመት በግማሽ ዓመቱ ያካናወኗቸውን ተግባራት እንደሚከተለው ማሳየት እንሞክራለን፡፡
የጥበቃ ደህንነት ስራዋችን በተመለከተ
በማረሚያ ቤቶች አስተማማኝ የጥበቃ ተግባር እንዲከናወን 6 ወሩ ውስጥ  2 ጊዜ ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ከዋናው ዕቅድ በተጨማሪ የጥበቃ ዕቅድ በማውጣትና ዕቅዱን ከሚፈጽመው የመለዩ ለባሸ አባላት ጋር ውይይት በማድረግ ከውጭ ሊደርስ የሚችለውን የጸረ-ሰላም ሀይሎችና ከውስጡ ሊከሰቱ  የሚችሉ ብጥብጦች አዳጋ ግምት ውስጥ በማስገባት በቋሚና ተንቀሳቃሽ የጥበቃ ዘዴ በቀንም ሆነ በማታ የጥበቃችን ተግባር ያላነዳች ችግር ተከናውኗል፡፡ ጥበቃውን በይበልጥ ለማጠናከር ከወቀቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በአመራሩ አቅጣጫ እየተሠጠ ከጥበቃ አባላት በተጨማሪ ሌሎች በስታፋ ተመድበው የሚሠሩ አባሎችን ተረኛ መኮነን በመመደብ የጥበቃ ደህንነታቸው እየተጠናከረ ይገኛል፡፡ ጥበቃ ለማጠናከር የፍተሻ ተግባሩን ልዩ ትኩረት በመስጠት 2 ቦታ በማድረግና ተግባረን እየተገመገመ በመምራት  ላይ ይገኛል፡፡
እንዲሁም ጥበቃ ከተለያዩ ስጋቶች ለማዳን የእሳት አዳጋ ግብረ ኃይል በማቋቋም ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡እንዲሁም ታራሚው ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረ ስለመጣ በከተማ አስተዳደሮችና  በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደሩ  ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች መኖሪያ ቦታ ጥበት ያለ ቢሆንም ታራሚዎችን በመኖሪያ ቤት አደረጃጀት በፍርድ ዓይነት በዕድሜ በመለየት የሚመደቡ ሲሆን የመስሪያ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ የጥበቃውን እንቅስቃሴ ለመቃኘትና የታራሚዎችን ችግሮች ለመፍታት የወረዳ ማረሚያ ቤቶችን ጨምሮ በአማካኝ 6ጊዜ ከታራሚዎች ጋር የውይይት መድረክ ተፈጥሯል፡፡ የእሳት ቃጠሎ መነሻ የሚሆኑ የተለያዩ ሁኔታወች ማለትም ሲጋሪ ማጨስ ምግብ የመከለስ ሁኔታዋችን ከታራሚው ጋር በግልጽ በመወያየትና በመግባባት በሁሉም ማረሚያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የማስቆም ሁኔታ ታይቷል፡፡ ወደ ተለያዩ ቦታዋች ታጅበው የሚወጡ ታራሚዋች ከስር እንዳያመልጡ ሆነ በፀረ-ሠላም ሀይሎች ጥቃት  እንዳይሰነዘርባቸው በጥበቃው መመሪያ መሠረት እንደታራሚዋች አደገኛነትና ባህሪ  እየታየ በጥንቃቄ እንደታጀቡ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡






ታረሚዎችን በእንጅባራ ማረሚያ ቤት ክሊኒክ ህክምና እየተደረገላቸው
የቅድመ መከላከል ሥራዎች በመስራት ላይ ቢሆንም በማረሚያ

ቤቶች ክሊኒክ ውል በተያዘው ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች አባላትና የአባላት ቤተሰብ ወንድ 393 ሴት 163 ድምር 556 ታራሚዎች ደግሞ ወንድ 3167 ሴት 165 ድምር 3332 የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የታራሚ ጠያቂ ዘመድ ወዳጆችን በተመለከተ
በህገ መንግስቱ በተረጋገጠላቸው መብት መሠረት የህግ ታራሚዋችን የጠየቁ ቤተሰቦች፣ጠበቆች እና የሀይማኖት አባቶች/በድግግሞሽ/ብዛት ወንድ 54064 ሴት 67041 ድምር 121105 የተጠየቁ የህግ ታራሚዋች/ በድግግሞሽ/ብዛት ወንድ 69972 ሴት2604 ድምር 72576 አንድ ፋይል ለአንድ ታራሚ በሚለው መርህ መሰረት ሁሉም ታራሚዎች የራሳቸው የግል ማህደር ያላቸው ሲሆን የሁሉም ታራሚዎች ፋይል ተደራጅተው ተይዘዋል፡፡
 







ታራሚዎች ከዘመጆቻቸዉ ጋር ሲጠያየቁ

የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል፡ ለታራሚዎችና ለህፃናት ምግብና በጀትን በማጣጣም  3ቱም ማረሚያ ቤት በአግባቡ እየተመገቡ ይገኛል፡፡ በምግብ አቅርቦት ሂደት ላይ ያሉ ችግሮችን በየቀኑ በመከታተል የማስተካከያ እርምጃ መስጠት ተችሏል፡፡ በንቃተ ህግ ትምህርት የተሰጣቸው በድግግሞሹ ወንድ 10550 ሴት 161ድምር 10711 የሥነ - ዜጋ ትምህርት የተሰጣቸው በድግግሞ ወንድ 4827 ሴት 124ድምር 4951 በማህበራዊ ኑሮ ትምህርት የተሰጣቸው ወንድ 10565 ሴት 103 ድምር 10668 በጋራ መድረክ በየወሩ ወንድ 5542 ሴት 104ድምር 5646 የማወየየት ሥራ ተሠርቷል፡፡

በማረም ማነፅ ዋና የሥራ ሂደት የተከናወኑ ተግባራት
· የህግ ታራሚዎች በእደ ጥበብ ሙያ አሰልጥኖ የሙያ ባለቤት ለማድረግ ወንድ 124 ሴት 4 በድምሩ 128ለማሰልጠን ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ወንድ 153 ሴት - በድምሩ 153 የህ/ታራሚዎችን ማሰልጠን ተችሏል፡፡ ይህም የዕቅዱን 120% ማከናወን ተችሏል፡፡
· በእንጨት ሥራ ወንድ 61ሴት- በድምሩ 61 ህግ ታራሚ ለማሰልጠን ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ወንድ88 ሴት- በድምሩ 88 የህ/ታራሚዎች በስልጠና ላይ ይገኛሉ፡፡ አፈፃፀሙም 144% ነው፡፡
· ኮንስትራክሽን ስልጠና ወንድ 94 ሴት 2 በድምሩ 96 ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ወንድ 110 ሴት -በድምሩ 110 ሲሆን አፈፃፀሙም 115% ማከናወን ተችሏል፡፡
· በግብርና ስልጠና ለመስጠት ወንድ 327ሴት 8 በድምሩ 335ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ወንድ 235 ሴት -በድምሩ 235ሲሆን አፈፃፀሙም 70% ነው፡፡
·  በመደበኛ ትምህርት ወንድ 351 ሴት 6 በድምሩ 357የህግ ታራሚን ለማስተማር ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ወንድ 357 ሴት 4 በድምሩ 361 የህግ ታራሚዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዕቅዱ አንፃር 101% ማከናወን ተችሏል፡፡
· መደበኛ ባልሆነ ትም/ ወንድ 140 ሴት 3ድምር 143 ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ወንድ 152 ሴት -ድምር 152 የህግ ታራሚዎች በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዕቅድ አንፃር አፈፃፀሙም 106% ነው፡፡
የህግ ታራሚዎች የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ ለወንድ 300 ለሴት 14 በድምሩ 314 የግል የምክር አገልግሎት ለመስጠት የታቀደ ሲሆን ለወንድ 222 ሴት 7በድምሩ 229 የህግ ታራሚዎች መስጠት ተችሏል፡፡ ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር 73% ነው፡፡ እንዲሁም ለወንድ 618 ለሴት 12 በድምሩ 630 የቡድን የምክር አገልግሎት ለመስጠት የታቀደ ሲሆን ለወንድ 437 ለሴት 20 በድምሩ 457 የህግ ታራሚዎች ለመስጠት ተችሏል፡፡

ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር 73% ነው፡፡







ታራሚዎች  በትምህርት ገበታ ላይ

ታራሚዎችን የተለያዩ መዝናኛዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የፑል፣ ካራንቡላ፣ ጆተኒ፣ የመረብ ኳስና የጠረጴዛ ቴንስ እንዲገባላቸው በማድረግ ለመዝናኛነትና ለገቢ ምንጭ ማስገኛ እንዲጠቀሙባቸው እየተደረገ ነው፡፡ እንዲሁም ታራሚዎች ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ በየቤታቸው ቴሌቪዥንና ዲሽ እንዲሟላና ሬዲዮ መጠቀም እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
· በሁለቱ የማረሚያ ቤቶች ገቢ ለማጠናከር 2008/2009 የምርት ዘመን 16.25 ሄክታር በሰብል ልማት ተሸፍኗል፡
·  42 በሬዎችን ለማድለብ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን 3ቱም ማረሚያ ቤቶች ብቻ 37 በሬዎችን ማድለብ ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙም 88 % ነው፡፡ 
·  14 የወተት ላሞች ዕቅድ ከተያዘው ውስጥ 13ላሞች ማርባት ተችሏል፡ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር 93% ነው፡፡
·  የንብ እርባታ ዕቅድ15 የተያዘ ሲሆን ክንውኑ 11 በዳንግላ ማረሚያ ቤቶች ብቻ  ተከናውኗል፡፡ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር 73% ነው፡፡
·  የመ/ቤቱን የውስጥ ገቢ ማሳደግ የተለያዩ የሰብል አይነቶችና የመስኖ ሥራዎች እየተሰሩ ሲሆን ቋሚና ጊዜያዊ አትክልቶችን ሙዝ፣ አኘል፣ ቡና፣ ሸንኮራ አገዳ በማስፋፋት ውጤታማ ሥራ በመስራት ላይ እንገኛለን፡


የማረም፤ ማነፅ፤ ሠራዊት አደረጃጀትን በተመለከተ
· የሲቪል ሠርቪስ ተቋምና የክልል ኮሚሽን ወረደው የአደረጃጀት ዕቅድ መሠረት የወረዳ ማረሚያ ቤቶችን ጨምሮ የአመራሩና የለውጥ አስተግባሪ 3 ቡድን  17 የሂደት ሠራተኞች አደረጃጀት 3 የጥበቃ አስተባባሪና ኦፊሰር አደረጃጀት፣  የጥበቃ አባላት አደረጃጀት 21 በማደራጀት ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በሁሉም አደረጃጀቶች ዕለታዊ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
·  እንዲሁም በታራሚዎች መካከል የሚሰራውን የማረምና ማነፅ ሥራዎችን ለማስቀጠል የወረዳ ማረ/ቤቶች ጨምሮ ጠቅላይ ኮሚቴ 4 ቀጠና ዞን 11 የመኖሪያ ቤት አስተባባሪ 31 የልማት ሠራዊት 138 በማደራጀት ወደተ ግባር ተገብቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡
· የማረም፣የማነፅና የሠራዊት ግንባታ በአባላት ክልሉ ካስቀመጠው አደረጃጀት አንፃር የተደራጀ ሲሆን በታራሚዎች መካከል 11 በማደራጀት የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡና ሁለንተናዊ ክትትል በማድረግ የወንጀልን አስከፊነት እንዲያወግዙ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡
· የማረም፣የማነጽ ሠራዊት አደረጃጀት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሠራተኛው ዘንድ እያስመዘገበ ያለው ለውጥ የሥራ ስዓት ማክበር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የተቀላጠፈ መሆን፣የሥራ ተነሳሽነት መናር  የሥራ ክፍተትን ቶሎ መሙላት፣ የቡድን ሥራን እንደባህል መቁጠር የመሳሰሉት ለውጦች አስመዝግቧል፡፡
· ታራሚው ያስመዘገባቸው መሠረታዊ ለውጦች የቡድን ሥራ ተግባብቶ መስራት፣ የውይይትን ባህል ማዳበር፣ የመረዳዳት ባህልን እንዲሁም የሚጠፉ ታራሚዎችን አጋልጦ በመስጠት እና ገንዘባቸውን በቁጠባ እንዲቆጥቡና ልማታዊ ተሳትፎአቸው እንዲዳብር አድርጓል፡፡ ሴቶች የህግ ታራሚዎችና ህፃናትን በተመለከተ፡-
·  ሴት የህግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲታረሙና የፀባይ ለውጥ እንዲያመጡ ክትትልና እንክብካቤ ይደረጋል፣ሴት የህግ ታራሚዎች በተለያዩ ሙያዎች ማለትም በሽመና፣ በታራሚ ቀለብ ማጥራት፣የጀበና ቡና እና ወጥ ሰርቶ ለታራሚው በማቅረብ ሥራ እንዲሳተፉናበአነስተኛ የንግድ ሥሪ ላይ ተሰማርተው   ገቢ እንዲያገኙ ተደርጓል፣ስርዓተ ፆታን በተመለከተ በህገ መንግስቱ ለሴቶች የተሰጠውን ልዩ ልዩ ድጋፍ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡
በሁሉም ማረሚያ ቤት የጀበና ቡና፣ የሸማ ስራና እደ ጥበብ  ሥራ ሴቶችን በማሳተፍ ገቢእንዲያገኙ ደርጓል፡፡
  የኤች አይ አገልግሎትን በተመለከተ፡-
· በዳንግላ ወረዳ ማረሚያ ቤት በተቋቋመው የሰራተኛች የጸረ ኤድስ ፈንድ አካኝነት 3 ወላጅ አልባ ህጻናት ድጋፋና እንክብካቤ እየተደረገላቸዉ ይገኛል፣የወረዳ ሆነ የዞን ሠራተኞች ሁሉም የኤች አይ ኤድስ ፈንድ አባል በመሆን የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፣ኤች አይ በደማቸው የተገኘባቸውን ሠራተኞችንና ታራሚዎችን እንክብካቤና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ በኤች አይ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ የአባሎች ልጆች ለወንድ 1 ለሴት 4፣በድምሩ 5 ህፃናት የዞን ኤድስ ፈንድ ታቅፈው በቋሚነት በየወሩ ለእያንዳንዳቸው ብር 100.00 በድምሩ 500.00 እየከፈላቸው ይገኛል፣
አካል ጉዳተኛን በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራት
በተጨማሪ ለአረጋዊያን አቅም ያላቸውን በሙያቸው እንዲሰሩና ገቢ እንዲያገኙ የሌላቸዉ ደግሞ የመስሪያ ቦታ ቅድሚያ ተሰጧቸው ሙያ ያላቸዉን ታራሚዎችእያሰሩ ገቢ እንዲያገኙ ተደርጓል፣ ለአካል ጉዳተኛች የተደነገጉ ህጐችናመመሪያዋች በተቋማችን እንዳይሸራረፍ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፣ ለአካል ጉዳተኛች ልዩ ትኩረት በመስጠት ያሉትን የአካል
 ጉዳተኞች በመለየት ታራሚዎችን ድጋፍናእንክብካቤ እየተደረገ ይገኛል ፡፡
·  በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ቅድሚያ ለአካል ጉዳተኛ  ታራሚ በመለየት የቀለም ማቅለም ስራ እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡
 





ታራሚዎች በሸማ ስራ ላይ
· ተቋሙ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት በማከናወን የተሻለ አፈፃፀም ቢያሳይም የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ችግሮች አጋጥሞታል፡፡የጥበቃ የፖሊስ አባላት የሰዉ ሃይል እጥረት መኖር፡፡
· በእንጅባራና በዳንግላ ተሸከርካሪ ባለመኖሩ ምክንያት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር መኖሩየጦር መሳሪያ ያለመሟላት፣
· የጤና ባለሙያ ያለመሟላት
ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች
· የጦር መሳሪያ በሚፈለገው መንገድ መሟላት አለመቻሉ፣ የሰው ኃይል እጥረት 3ቱም ማረ/ቤት የፖሊስ አባላት እና የህክምና ባለሙያ ያለመሟላት፣የቻግኒ ወረዳ ማረ/ቤት የግንባታ ቦታ መፍትሄ ያለማግኘት፣በዳንግላ ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ የታራሚዎች ወፍጮ ማስፈጫ ያለመኖር እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ውድ አንባቢያን መንግስት ዜጎችን ከማረም እና ከማነፅ ባሻገር ከልማቱ ዕድገትም ጎን እንዲሰለፉ እያደረጋቸው መሆኑን ማሳየት ሞክረናል፡፡ ስለሆነም ይህ ተግባር ለመንግስት ብቻ የሚተው ስላልሆነ ሁሉም ዜጋ ከመንግስት ጎን በመቆም ወንጀል እንዳይፈጸም ቀድሞ በመከላከልና  በአገር ዕድገት ላይም ርብርብ ማድረግ ይገባናል እንላለን፡፡
                    ምንጭ፤ እንጅባራ ማረሚያ


No comments:

Post a Comment