ከታላቁ የህዳሴ
ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 6ኛ ዓመት በዓል ጋር በማስተሳሰር ሲካሄድ የነበረው የአዊ ብሔረሰብ የባህል ፌሲቲባል ተጠናቀቀ፡፡
የአዊ ብሔረሰብ
አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ያዘጋጀው ይህ የባህል ፌሲቲባል ሲዘጋጅ ለሁለተኛ ሲሆን ነው፡፡ በፌስቲባል ንግግር ያደረጉት
የብሔ/አስ/ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ባይነሳኝ ካሳሁን የብሔረሰቡ ማንነት መግለጫ የሆነው ባቱ ባህል፣ቋንቋ ታሪክና ቅርስ
በመጪ ባህል እየተበረዘ በመሆኑ ከእታዊ መጤ ባህሎች የመታደግ ሁላችንም ኃላፊነት አለብን፡፡
የዚህ ፌስቲባል
መካሄድ ዋና ዓላማውም የየአካባቢያቸውን ባህል ይዘው የመጣ ተሳታፊዎች እርስ በእርስ ልምዳቸውን የሚለዋወጡበትና ተተኪ ከያንያንን
ለማደራጀትም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
ከፌስቲባሉ ተሳታፊዎች
መካከል አበበ ወርቁ እንደተናገረው በየወረዳው ያሉ አማተር ከያንያንን እርስ በእርስ ልምድ እንድንለዋወጥ ከማስቻሉ ባሻገር በብሔረሰብ
አስተዳደሩ ብዙ ያልተነሱ ባህሎች ያሉ ስለሆነ አጉልቶ ለማሳየትና ጥንታዊ ባህላችንን ጠብቀን ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ኃላፊነት
እንደሚጠበቅብን ያሳየነው ብሏል፡፡
በፌስቲባሉ 12
የባህል ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በተሰጣቸው መስፈርቶች በመወዳደር የአዊ ባህልና ኪነ ጥበባት ቡድን አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡ ይህ
ቡድን በክልል ደረጃ በሚደረገው የፌስቲባል ውድድር ብሄረሰብ አስተዳደሩ ወክሎ የሚሳተፍ እንዲሆንም ተናግረዋል፡፡
No comments:
Post a Comment