በአዊ ብሔ/አስተዳደር እንጅባራ ከተማ በፌደራል መንግስት የተገነባዉ ድልድይ የህብረተሰቡን ጥያቄ ያልመለሰ መሆኑን የከተማዉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ ብሔ/አስተዳደር ከእንጅባራ - ጉባ የሚወስደዉ የአስፓልት መንገድ በእንጅባራ ከተማ የተነገባዉ መንታ ድልድይ ስታንዳርዱን ያልጠበቀ በመሆኑ ምክንያት የጎርፍና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ እየሆነ ነዉ ሲሉ ከከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ተናግረዋል፡፡
ከነዋሪዎቹ መካከል በሰጡት አስተያየት የዚህን ድልድይ ችግር ለሚመለከተዉ አካል በተደጋጋሚ ብናመለክትም ምላሽ አልተሰጠንም በአሁኑ ስዓት ቀላል ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት በጎርፍ ድልድዩ በመሙላት ለአሽከርካሪዎችና ለመንገደኞች አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ድልድዩ የተሰራዉ ከአርባ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ተጨማሪ አዲስ የተሰራዉ ድልድይ የመጀመሪያዉን መሰረት አድርጎ በመሆኑ የጎርፍ መጥለቅለቅና የመኪና ቅጭቶች እየተፈጠረ ነዉ፡፡ መንግስት የዚህን መንገድ አስፈላጊነት ግምት ዉስጥ በማስገባትና ድልድዩ ጥራቱን ጠብቆ ባለመሰራቱ ምክንያት አሁን ላይ የሚስተዋለዉን ችግሮች ለመፍታት እንደገና ፈርሶ መሰራት እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡
የአዊ ብሔ/አስተዳዳሪ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየን ብርሃን ሰለ ጉዳዩ ተጠይቀዉ በሰጡት አስተያየት የድልድዩ ግንባታ የጥራት ችግር ያለበት መሆኑን አረጋግጠዉ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ከህዝቡ፣ ከአመራሩና ከባለሙዎች ጋር ዉይይት በማድረግ ወደሚመለከተዉ አካል በተደጋጋሚ ድልድዩ ተስተካክሎ እንዲሰራ እየጠየቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

No comments:
Post a Comment