በአዊ ብሔ/አስተዳደር ለ7 ጊዜ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከባለሃብቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡
በአዊ ብሔ/አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ነጋ እንግዳ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በብሔረሰብ አስተዳደሩ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች በ3ቱ ከተሞች ማለትም በእንጅባራ፣ በቻግኒና በዳንግላ ከተሞች 357 ሄ/ር መሬት የማካለል ስራ መሰራቱን ጠቁመዉ በመንግስት ተቋማት የለማ ቦታ አዘጋጅቶ ቀልጣፋ አገልግሎት አለመስጠት፣ መሰረተ ልማት ያለማሟላትና የመብራት መቆራረጥ እንዲሁም የብድር ስርዓት አለመመቻቸት እና ሌሎች ችግሮች በዘርፉ ይስተዋላሉ፡፡ መሬት አጥረዉ የተቀመጡ ሁለት ባለሃብቶችንም የመንጠቅ እርምጃዎች ተወስደዋል ያሉት ኃላፊዉ በቀጣይ ችግሮችን በመፍታት ኢንቨስትመንቱን ለማጎልበት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በብሔ/አስተዳደሩ በዚህ ዓመት 28 ቢሊየን 103 ሚሊየን 002 ሺ 530 ብር ካፒታል ላስመዘገቡና ለ238 ሺ 396 ዜጎች የስራ እድል ሊፈጥሩ የሚችሉ 1 ሺ 99 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥም 250 ፕሮጀክቶች ምርት ማምረት ላይ የሚገኙ ሲሆን ለ28 ሺ 245 ዜጎች የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡ በአምራች ኢንዱስትሪ ተሰማርተዉ ማምረት የጀመሩ ደግሞ 6 ፕሮጀክቶች መሆናቸዉን አቶ ነጋ ገልፀዋል፡፡


No comments:
Post a Comment