Tuesday, 17 February 2015

ስለ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ወቅታዊ መረጃ


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ 8 ዞኖችና 3  ብሔረሰብ አስተዳደሮች መካከል የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አንዱ ነው፡፡  /አስተዳደሩ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩለትም 1987. ሲሆን 1ሚሊዮን 1 መቶ ሽህ የሚበልጥ ህዝብ የሚኖርባት፣ 837 886/ የቆዳ ስፋት፣ 75% ይና ደጋ 25% ደጋና ቆላ የአየር ንብረት ባለቤት 180 የገጠር 22 የከተማ ቀበሌዎችም አሏት፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር የሚወስደው አስፖልት መንገድ ካሏት 8 ወረዳዎችና 3 የከተማ አስተዳደሮች መካከል 4 ወረዳዎችንና ሁለት ከተማ አስተዳደሮችን መሃል ለመሃል አቋርጦ ያልፋል፡፡ የብሔ/አስተዳደሩ ርዕሰ ከተማ እንጅባራ ከአዲስ አበባ 435 / ከክልላችን ርዕሰ ከተማ ባህር ዳር 118 / ብቻ ትርቃለች፡፡ እየተገነባ ካለው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ደግሞ 286 . ያልበለጠ እርቀት ይገኛል፡፡በብሄረሰብ አስተዳደሩ ጃዊ ወረዳ 3 የመንግስትና 1 የግል የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታዎች እየተፋጠነ ይገኛል፡፡
ብሄ/አስተዳደሩ ተቀድቶ የማያልቅ ባህል የራሱ የሆነ ቋንቋና በኢትዮጵያ ታሪክ አስተዳደራዊ ድርሻ የነበረውና ቀደምት ህዝብ ነው፡፡ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ከአዊኛ በተጨማሪ አማርኛ በስፋት ጉምዝኛና ሽናሽኛ በጥቂቱ የሚነገርበት፣ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችም ተከባብረውና በነፃነት የሚኖርባት አስተዳደር ነው፡፡
አዊ የበርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህብ ሃብቶች ባለቤትም ነው፡፡ የዘንገናና የጥርባ ሃይቅ፣ የትስኪ፣ የዶንደር፣ የፋንግና የጋርቾ ፏፏቴ፣ የዳንጉላ ዋሻና የወለተ ጴጥሮስ ገዳምን በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡ የአዊ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ያበረከተውን የአስተዳደርና የስልጣኔ ታሪኩን ያህል ባለፉት መንግስታት ቦታ ሳይሰጠው ቀርቶ ቋንቋውና ባህሉ ተዘንግቶ ቆይቷል፡፡ይሁን እንጂ  ከዛሬ 20 ዓመት በተለይም ራሱን በራሱ እንዲስተዳድር ህገ-መንግስታዊ መብቱን ከተጐናፀፈበት ጊዜ ጀምሮ በልማት በመልካም አስዳደርና  በባህል
ዘርፍ ውጤት እያስመዘገበ ያለ ብሄ/አስተዳደር ነው፡፡ 
የብሔ/አስተዳደሩ ህዝብ በርካታ ነባር የሆኑ የግብርና ስራዎች ልምድ ባለቤት ነው፡፡ ለእርሻ የሚሆን ለምና ሰፊ መሬት ያለው ከመሆኑም በላይ ለተለያዩ የግብርና ዘርፎች አመችም ነው፡፡ በአንፃራዊነቱ ለምነቱ አናሳ ነው ተብሎ የሚታሰቡት ደጋማዎቹ አካባቢዎት እንኳ በቂ ዝናብ የሚያገኙ በመሆናቸው ክረምት እስከ በጋ በገጸ ምድርና በከርሰ መድር ውሃ የበለጸጉ  ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ በየአካባቢው ለሚለማው ጊዜያዊ አትክልትና ቋሚ አትክልቶች ለማልማት ምቹ ነው፡፡ ለዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለመደ የመጣውንና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረገውን የአፕል ምርት ተጠቃሽ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ብሔ/አስ በባህላዊ መስኖ ሥራም ሰፊ ልምድ ያለው ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች አርሶ አደሩ በባህላዊ መንገድ የሠሯቸው ባህላዊ መስኖዎች የሚደነቁ ናቸው፡፡ብሔረሰብ አስተዳደሩ በብዛት በበርበሬ፣በማርና በሰሊጥ ምርት ይታወቃል፡፡
ብሔ/አስተዳደሩ በትምህርቱ ዘርፍም ስንመለከት ዜጐች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ህገ-መንግስቱ በግልፅ ባስቀመጠው መሠረት 1989 / መሰጠት የጀመረው የአዊኚ ትምህርት በኮሌጅ ደረጃም መምህራን በቋንቋቸው ሠልጥነው እያስተማሩበት ይገኛል፡፡ በሁሉም ወረዳዎች የከፍተኛ 2 ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት እየተሰጠ ሲሆን 1 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባለቤትና በዚሁ ኮሌጅ አስተባባሪነት 5 ክላስተር ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ይገኙበታል፡፡  
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በክልላችን ትርፍ አምራች ከሆኑ ጥቂት ዞኖች አንዷ ስትሆን ለቤት እንስሳት እርባታናማድለቢያና ለንብ ማነብ አመቺ በመሆኗ አርሶ አደሩ በሁሉም የግብርና ዘርፎች ተጠቃሚ ነው፡፡ በተጨባጭ የብ/አስተዳደሩ ለምነት ያለው ሰፊ መሬት፣ በቂ
ዝናብና እርጥበት፣ ርካሽ ጉልበት የባህላዊ መስኖና የተለያዩ እንስሳት ተጠቅሞ የማረስ ነባር ልምድ ያለው አርሶ አደር መገኛ  ብሔ/አስተዳደር ነው፡፡የብሔ/አስተዳደሩ ወጣቶችና ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ የከተማ ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ቤቶች ልማት ከተማ ግብርና መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በተፈጠሩ የስራ እድሎች በመሠማራት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡በ2006 በጀት ዓመት በከተማ ብቻ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ64ሽ በላይ ወጣቶች ወደ ስራ ማሰማራት ተችሏል፡፡ በገጠርም እንዲሁ በግብርና ስራ በመደራጀት  በተለያዩ ዘርፎች ተሠማርተው ራሳቸውንና ቤተሰብንም እየጠቀሙ ይገኛሉ፡፡  ሴቶችም በተለያዩ አደረጃጀቶች ታቅፈዉ ስለመብታቸዉና ተጠቃሚነታቸዉ  ከመምከራቸዉም በላይ ከወንዶች ባልተናነሰ ራሳቸዉን በስራ ጠምደዉ በርካታ ሴቶች ሃብት ማፍራት ጀምረዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ለመብታቸዉ የሚታገሉና የሚያስከብሩ ሞጋች ሴቶችም  መበራከት ጀምረዋል፡፡
በብሔረሰብ አስተዳደራችን 70 ዓመታት በላይ ዕድሜ  ያለው አለም የሰባት ቤት አገው ፈረሰኛ ማህበር ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአዊ ባህላዊ ጋብቻ እና የመስቀል በዓል አከባበር የዞኑ መልካም መገለጫዎች ናቸው ፡፡በብሔረሰብ አስተዳደሩ ከዳንግላ እስከ ቲሊሊ ከተማ ባለው አስፖልት መንገድ እና በከተሞች ውስጥ በርካታ የህ/ሰብ ክፍሎች ባህላዊ የቱሪስት የስጦታ ዕቃዎችን ከቅርቀሃ፣ ከቆዳ፣ በሽመና፣ በጭራ፣ በዋንጫና በጥልፍ ውጤቶች እያመረቱ በመሸጥ ላይ ይገኛሉ፡፡
የብሔ/አስተዳደሩን ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ የሚያስተዋውቅ የአዊ ባህልና ኪነ-ጥበባት ማህበር ተቋቁሞ በአዊ ልማት ማህበርና በብሔ/አስ//ቤት የገንዘብ ድጋፍ እንተዋወቅ ቁጥር 1 እና 2 የኦዲዮና ቪሲዲ ካሴት አልበሞች ተሠርተው ብሔ/አስተዳደሩን በሃገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ በሚገባ አስተዋውቋል፡፡በአዊ /አስተዳደር ባለፉት 23
አመታት በጤናዉ ዘርፍ በተደረገዉ ፈርጀ ብዙ ርብርብ የጤናዉ ዘርፍ እምር አሳይተቷል41 ጤና ጣቢያዎች፣ 181 ጤና ኬላዎች፣ 1ሽ 444 በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ይዞ ሁሉም የገጠር አካባቢዎች በማማከር የጤና አገልግሎት ሽፋኑን 98.4% አድርሷል፡፡ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎች በመገንባት ላይ ሲሆኑ የእንጅባራ ዞናል ሆስፒታል 107 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ሲገኝ በግምጃቤት ከተሞችም የወረዳ ሆስፒታሎች ግንባታቸው በመተናቀቅ ላይ ነው፡፡ ባለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በብሔረሰብ አስተዳደሩን ዝብ መንግስትና ረጅ ድርጅት አማካኝነት በቻግኒና በዳንግላና በእንጅባራ 3 ትልልቅ ጥልቅ የውሃ ተቋማት ግንባታ  ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የዳንግላ ከተማ ውሃ ተቋማት ግናባታው ተጠናቆ አገልግሎት  መስጠት ጀምሯል፡፡በብሔ/አስተዳደሩ በርካታ የማዕድን ሃብቶች የሚገኙ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ እብነ በረድ፣ የማዕድን ውሃ፣ ፍልውሃ፣ ወርቅ፣ የድንጋይ ከሰል፣ የኖራ ድንጋይ፣ ሬዳሻ፣ ቀይ ሸክላ አፈር፣ የግንባታ አሸዋና ብረት ይገኙበታል፡፡
በብሔረሰብ አስተዳደራችን በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች 24 ሰዓት የመብራት እና የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሁነዋል ፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና የውሃ ማፋሰሻ ቦዬችም  በመገንባታቸው ከተሞች የተሻለ አገልግሎት እያገኙ ናቸው፡፡ በክልሉ መንግስት አማካኝነት ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት የመንገድ ፕሮግራም ዝርጋታም በገጠር እየተፋጠነ ነው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ለኮብልስቶንና ለቤቶች ስራ የሚያገለግል የሸድ ስራ፣ በከተሞች የኮብልስቶን ማንጠፍ ስራ ተጀምሯል፡፡ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በሚገኙ 8 ወረዳዎችና 3 የከተማ አስተዳደሮች የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረውን የመኖሪያ ቤት እጦት ችግር ለመቅረፍ ከክልል በተፈቀደው መሰረት ከ250 በላይ ለተደራጁ ማህበራት ወይም  ከ4ሽ በላይ ግለሰቦች የቤት
መስሪያ ቦታ ተሰቸው በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ከዚህም በተጨማሪ  በእንጅባራ ከተማ 800 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተሠርተው ለተጠቃሚ ተላልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ ብሔ/አስተዳደራችን ለምነቱ ያልተካ፣ ለሁሉም የልማት ስራችን ማንኛውም አካባቢውን አልምቶ ራሱን መለወጥ የሚፈልግ አካል ቢመጣ ያለምንም ቢሮክራሲ የሚያስተናግድበት ነውና ይምጡ
አካባቢውን ያለሙ እርስዎም ከፀጋው ይጠቀሙ፡፡ ደግሞም እርስዎ ተጠቅመው ፀጋው የሚያልቅ አይደለምና ሌሎችም ከዚህ በረከት ይቋደሱ ዘንድ አካባቢያችንን ፍንትው አድርገው ይንገሯቸው፡፡ ከህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት እስከ አስተዳደሩ አመቻችነት ድረስ ያለምንም ውጣ ውረድ ይስተናገዳሉና፡፡