Tuesday, 29 May 2018

















ምህርት ጥራት መሰናክሎች ለመጭው ሀገር ተረካቢ ትውልድ በሽታ ናቸው!!
ትምህርት የእድገት ሁሉ መሰረት ነው፡፡ምክንያቱም ትምህርት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ እሴቶችን ለማዳበርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ለማጠናከር የአመለካክት ለውጥ ለማምጣት ቁልፍ መሳሪያችን ስለሆነ፡፡ትምህርት የአመለካከትና የአስተሳስብ  አድማስን በማስፋት የምርምርና የፈጠራ ችሎታን በማዳበር፣ ለምርትና ምርታማነት መጨመር  እንዲሁም የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማፋጠን የሚያስችል ወደር የለሽ ሚና ያለው ነው፡፡
መንግስት ትምሀርት ለልማት ፣ለሰላም፣ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር ችግር መፍቻ ቁልፍ  ሚና  የሚጫወት መሆኑን በውል በመገንዘብ  እና ለዘርፉ እድገት  ልዩ ትኩረት በመስጠት በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎች ሰብዕናው በተሟላ መንገድ በእውቀት፣በክህሎት፣በመልካም ስነ-ምግባር እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ እሴቶችንና መርሆችን የተገነባ ዜጋ ማፍራት የሚያስችል የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ቀርፆ በስራ ላይ አውሏል፡፡ከፍተኛ መዋለ ንዋይ መድቦ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመዘርጋት እና የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
በብሔረሰብ አስተዳዳሩ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከዚህ በፊት በየዓመቱ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በክልሉና በአገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ስለሆነም በ2010 በጀት ዓመት 10ኛ እና 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ  ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች 10ኛ ክፍል በ34 ትምህርት ቤቶች ወንድ  9,221 ሴት 11,185 በድምሩ 20,406 ሲሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ20 ትምህርት ቤቶች ወንድ 2,726 ሴት 2,650 በድምሩ 376 ተማሪዎች አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ይሁን እንጂ የትምህርት ጥራት መሰናክሎች በርካታ ሲሆኑ እንደ ብሔረሰብ  አስተዳደር የተለዩት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.  የትምህርት ግብዓቶች በወቅቱ አለመሟላት
2. የትምህርት ጥራት መርሃ ግብሮችን በአግባቡ በትምህርት ቤቶች ላይ  አለመተግበር
3. ተማሪዎችን በተገቢው መንገድ አለመመዘን
4. የመብራት መቆራረጥና ከእነጭራሹ አለመኖር
5. የኩረጃ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ መዳበር
6. የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች  ደረጃውን  ሳያሟሉ መከፈት
7.የትምህርት አመራሮች የአመለካከት ችግር መኖርና የመሳሰሉት የትምህርት ጥራት መሳናክሎች ናቸው፡፡
1.የትምህርት ግብዓቶች በወቅቱ አለመሟላት
የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ ግብዓት ወሳኝ ነው፡፡ይኸውም አዳዲስ ትምህርት ቤቶችና በገጠር አከባቢ የሚገነቡ ት/ቤቶች የፕላዝማና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን አለመሟላት፣የቤተ-መጽሐፈፍት ቁሳቁሶችና የተማሪዎች ማስተማሪያ መጽሐፍ በወቅቱ አለመመደብ፣የሰው ሀይል እጥረትና በሙያው የሰለጠኑ መምህራን በሰለጠኑበት ሙያ አለመመደብ ችግር ናቸው፡፡
2. የትምህርት ጥራት መርሃ ግብሮችን በአግባቡ በትምህርት ቤቶች ላይ  አለመተግበር
የትምህር ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆች ስድስት መርሀ ግብሮች ያሉት ሲሆን እነዚህ መርሀ-ግብሮች በትክክልና በተገቢው መንገድ በት/ቤቶች በመተግበር የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ መርሀ-ግብሮችን በትምህርት ቤቶች ላይ  በተገቢው መንገድ አለመተግበር የሚያመጣው ችግር ነው፡፡ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ መርሃ ግብሮች ስርዓተ-ትምህርት መርሃ ግብር፣መምህራን ልማት መርሀ-ግብር፣ስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መርሃ ግብር ፣ኢንፎርሜሽን ኮሚኒከሽን ቴክኖሎጂ መርሀ ግብር፣የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀ ግብር እና የትምህርት ቤት አመራርና አስተዳደር መርሀ ግብር ናቸው፡፡
3. ተማሪዎችን በተገቢው መንገድ አለመመዘን
ከትምህርት ጥራት እንቅፋቶች አንዱ ተማሪዎችን በተገቢውና በሚያውቁት ልክ አለመመዘን ሲሆን ይህም መምህራን ለተማሪዎች የተከታታይ የምዘና ውጤት በግምትና በግዴልሽነት እንዲሁም ሀላፊነት በሚሰማው መንገድ ውጤት ያለመስጠት ችግር ነው፡፡
4.የመብራት መቆራረጥና ከእነ ጭራሹ አለመኖር
መንግስት የትምህርት ሽፋኑን ተደራሽና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ተግባራዊ ለማድረግ በከተማና በገጠር ወረዳዎች በርካታ 2 ደረጃ እና መሰናዶ /ቤቶች ተገንብተዋል፡፡
በገጠር አካባቢ በሚገነቡት /ቤቶች የመብራትና የሌሎች መሰረተ ልማቶች ተደራሽነት ባለመኖሩ ተማሪዎች የፕላዝማና ሌሎች  የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ወስደው ተወዳዳሪ አለመሆን መሰረታዊ ችግር ነው፡፡
5 የኩረጃ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ መዳበር
ተማሪዎች ጊዜዊ ተስፋ በማድረግና በራስ አለመተማመን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በቂ የትምህርት ዝግጅት ያላደረጉ ተማሪዎች ከጎበዝና በራስ የሚተማመኑ ተማሪዎች ላይ በመኮረጅ ፈተና እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡
በተለይም ጥቂት ሃላፊነት የማይሰማቸዉ የትምህርት አመራሮች የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላይ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው በመኮራረጅ ከፍተኛ ውጤት እንዲያመጡ ድጋፍ ይደረጋሉ፡፡ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያመጣው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ት/ቤት ተሸላሚ ስለሚሆን፡፡ከዚህ በተጨማሪ በራሳቸው የማይተማመኑ አንዳንድ ተማሪዎች ፈተናን ለመኮረጅ እንዲመቻቸው የጎበዝ ተማሪዎች  ስም ጋር ለማመሳሰል በፍርድቤት ስም  የመቀየር በስፋት የሚታይ በሽታ ነው፡፡ይህ የኩረጃ ባህልና የስም መቀየር እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር የከፋ ቸህግር እየሆነ መጥቷል፡፡
6.የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ሳያሟሉ መከፈት
መንግስት የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ ሲባል በየአካባቢው የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች የመመዘኛ ደረጃ ሳያሟሉ በየገጠር ባሉ ወረዳዎችና መሰረተ ልማት ሳያሟሉ መከፈት አንዱ የትምህርት ጥራት ችግር ነው፡፡
7.የትምህርት አመራሮች የአመለካከት ችግር መኖር
የትምህርት አመራሮች የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ በመሆን የትምህርት ተቋማትን አለመምራት፡፡
 በተለይም 10ኛ እና 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች መሰረት ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም በግምት ውጤት በመስጠትና በመኮራረጅ ተመሳሳይ ውጤት እንዲያመጡ በማድርግ የመጭውን ሀገር ተረካቢ ትውልድ በትምህርት የታነፀ በስነምግባሩ የተስተካከለ እንዲሆን አለማድረግ፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ትምህርት ዋና መምሪያ የትምህርት ጥራት መሰናክሎች ለማስወገድ በ2010 በጀት ዓመት እያደረገ የለው የቅድመ ዝግጅት ዕርምጃዎች
 መምሪያው የትምህርት ጥራት መሰናክሎች  ለመቅረፍ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ለ10ኛ እና ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን በራስ የመተማመን መንፈስ ኑሮቸው ተረጋግተው ፈተና እንዲወስዱ የሚከተሉትን ስልቶች ቀይሷል፡፡
1. የወላጆች፣የተማሪዎችና የትምህርት ባለድርሻ አካላትን መድረክ በመፍጠር የግንዛቤ ትምህርት መስጠት መቻሉ
2. በ36 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣በ157 ሱፐርቫይዘሮችና በ501 ፈተኝ መምህራንና ለትምህርት አመራሮች ኦረንቴሽን በመስጠት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ከማድረግ ባሻገር ጎበዝ/በራሳቸው የሚተማመኑ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲፈተኑ የብቻቸውን ተለየተው እንዲፈተኑ ማድረጉ
3. በራሳቸው የማይተማመኑ ተማሪዎች ከጎበዝ ተማሪዎች የስም ማመሳሰል እንዳይደረግ ከዳኞች ጋር ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ማድረጉ
4. በአጠቃላይ ተማሪዎች በራስ በመተማመን ተረጋግተውና ተገቢውን ዝግጅት አድርገው ፈተና እንዲወስዱ ከባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት ላይ መድረስ መቻል፡፡











Thursday, 22 March 2018

የዙራሙሪ  መጽሄት የእንግዳ አምድ አንባቢዎቻችን እነሆ በዚህ የአከባቢ ህትመት እትማችን  በአንድ ወቅትከኦሮሚያ ክልል ወደ አዊ ብሔ/አስ ከቤተሰቦች ጋር በመምጣት በንግድ ስራ በመሰማራት ስኬታማ ከሆነው ከአቶ ይስማው አለማየሁ ጋር ቆይታ አድርገናል መልካም ንባብ፡፡
ዙራሙሪ ፡- የትውልድ ቦታ እና እድሜ ?
አቶ ይስማው፡- ዕድሜየ 40 ሲሆን የተወለድኩበት ኦሮሚያ ክልል ወለጋ ክፈለ ሀገር ጊምቢ ከተማ ነው፡፡
ዙራሙሪ፡- የትምህርት ደረጃህ ? የምትኖርበት አካባቢ ?
አቶ ይስማው፡- እስከ 10 ክፍል ዘልቄለሁ፡፡በእንጅባራ  ከተማ ነው የምኖረው፡፡
ዙራሙሪ፡- እንዴት ወደ አማራ ክልል አዊ ብሔ/አስ መምጣት ቻልክ ?
አቶ ይስማው፡- ተወልጄ ያደኩት ጊምቢ ከተማ ሲሆን 1988 . በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ተፈናቅለን ወደ ጎጃም መምጣት ችለናል፡፡ወደ ጎጃም የመጣሁትከእናት አባቴ እንዲሁም  ከእህት ወንድሞቼ ጋር ነው፡፡
ዙራሙሪ፡- ለቤተሰብ ስንተኛ ልጅ ነህ ? አዊ ብሔ/አስ አዘና ከተማ ስትገቡ ምን ይዛችሁ ነበር የመጣችሁት ?በምን ስራሰ ቤተሰቦችህ ተሰማሩ ?
አቶ ይስማው፡- ለቤተሰቦቼ 3ተኛ ልጅ ስሆን ምንም አይነት ሀብትና ንብረት ይዘን አልመጣንም ፡፡ሀብታችንና ንብረታችን በግርግሩ ምክንያት እዛው ነበር ትተን የመጣነው፡፡
አባቴ በገምቢ ከተማ ነጋዴ ሰለነበረ ወደ አዊ ብሔ/አስ ስንመጣም ንግድ መሞከር ጀመረ፡፡በ1990  10 ክፍል ላይ አቋርጨ ከሀብታሞች ብር በመቀበል እሁዲት ሚዛን ዘርግቼ  ጤፍ፣ሰሊጥ፣በቆሎበመግዛት  መልሼ ለሀብታሞች በማስረከብ ጀመርኩኝ ፡፡በዚያን ግዜ እድሜየ 20 ሲሆን ምንም ነገር ያልነበረን በመሆኑ ቤተሰቦቼን እና  እኔን በጀመርኩት ችርቻሮ አስተዳደር  እና ተናናሾቼን አስተምር  ነበር፡፡
                         አቶ ይስማው
ዙራሙሪ፡- ወደ አዊ ብሔ/አስ ስትመጡ እንዴት ነበርህዝቡ የተቀበላችሁ ?
አቶ ይስማው፡- በአዊ ብሔ/አስ ሁሉም ብሔረሰቦች የሚኖርበት ስትሆን እኛንም ያለምንም ችግር ተቀብለውናል ፡፡አዊ ብሔ/አስ በአብሮነት በመኖር ፣ለኑሮ ተስማሚ ፣ሰው የሚከበርበት ውብ አካባቢ ነው፡፡
ዙራሙሪ፡- ወደ እርሻ ኢንበስትመንት  እንዴት መሰማራት ቻልክ ?
አቶ ይስማው፡- በንግድ ስራ እየተጠናከርኩ ስመጣ 1997 . አንድ አስመጪና ላኪ ደንበኛችን እንድ አይሱዝ ሙሉ ሰሊጥ ይዞብኝ ጠፋ፡፡በዚህ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወረቴን ይዞ በመጥፋቱ የከሰርኩበት ዘመን ነበር፡፡ምንም ባልነበረኝ በዚህ ወቅት  ግንቦት ወር ላይ በማህበር እርሻ  መንግስት ፈቀደልን፡፡ እርሻው 4 ሁነን እንድናርስበት 83 / መሬት የተፈቀደልን ሲሆን ከእኔ ዘንድ ምንም አይነት ገንዘብ  አለመኖሩን አውቀው  መሬቱን መከፋፈል አለብን ብለው  ወሰኑ፡፡ምንም እንኳህጉ ባይፈቅደውም መሬት ተከፋፍለን እርሻ ጀመርነ፡፡ እነሱ 10 ዕቃ በሬ ሲደርሱ እኔ  የሰው ፍቅር እና  እምነት ስለነበረኝ 5 ዕቃ በሬ ማረስ ቻልኩ፡፡በ1999 . እነሱ በበሬ ሲያርሱ እኔ በትራክተር  በማረስ እየተጠናከርኩ መጣሁ፡፡
ዙራሙሪ፡- መቼ ነበር በጋር በማርስ አባይጠጆ  እርሻ ልማት የመሰረታችሁ ?
አቶ ይስማው፡- 2000 . ከአንድ አባላችን በስተቀር  3ሁነን 83 / መሬት ላይ በጋራ ሰሊጥ፣ በርበሬ ፣በቆሎ እና ማሾ ማምረት ችለናል፡፡
እርሻችን በረሃ አካባቢ እና የሰጡትን ሁሉ የሚያመርት በመሆኑ ምርታማነትን ማሳደግ በመቻላችን ተጠቃሚ ሁነናል፡፡
ዙራሙሪ፡- በሄክታር ምን ያህል ምርት ታገኛላችሁ ?
አቶ ይስማው፡- አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ በመሆናችን በቆሎ 80 ኩንታል እና በርበሬ  እስከ 30 ኩንታል እናገኛለን ፡፡
                   የአቶ ይስማው መኖሪያ ቤት
ዙራሙሪ፡- በጋራ መስራት ያለው ጠቀሜታ  ?
              
አቶ ይስማው፡- በጋራ መስራት ምርታማነትን ማሳደግ ከመቻሉም በተጨማሪም በጋራ ለማደግ ያስችላል፡፡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
ዙራሙሪ፡- አባይ ጠጆ እርሻ ልማት አሁን ላለህበት ስኬትህ ምን ድርሻ ነበረው ?
አቶ ይስማው፡- ለኑሮየ መቀየር እርሻው ባለውለታየ ነው፡፡
ዙራሙሪ፡- መቼ ነበር ወደ  እንጅባራ ከተማ  የገባኸው ?ወደ ከተማ የመግባት ምክንያትስ?
አቶ ይስማው፡- የዕድሜየን ግማሽ በረሃ ነበር የኖሩኩት፡፡እሁዲት  3 ልጆችን ወልጀ ሀብት ንብረት ያፈራሁበት አካባቢ ሲሆን በበረሀ ያፈራሁትን ሀብት በብሔ/አስ እንጅባራ ከተማ ኢንቨስት  ፍብሪካ ለመገንባት ዕቅድ  ይጄ 5 ዓመት በፊት ከተማ ገብቻለሁ፡፡
ዙራሙሪ፡-   በብሔ/አስተዳደሩ ፍብሪካ በመገንባት በቅድሚያ ወደ ስራ  የገባህም አንተነህ ይባላል ?
አቶ ይስማው፡- እውነት ነው 5 / መሬት መንግስት ባመቻቸልኝ በከተማው ስንዴ የዱቄት ፋብሪካ ግንባታ በጀመርኩት በአንድ አመት ተኩል  ውስጥ ማምረት ችያለሁ፡፡
ዙራሙሪ ፡-  በምን ያህል ካፒታል ፋብሪካው ተገነባ ?
አቶ ይስማው፡- ዘንገና ሃይቅ የዱቄት ፋብሪካ 20 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን በቀን 620 ኩንታል የስንዴ ዱቄት መፍጨት ይችላል፡፡
ዙራሙሪ፡- በፋብሪካው የስራ ዕድል ፈጠራው እና ምን ያህል ደመወዝ ይከፈላቸዋል ?
አቶ ይስማው፡- 18 ቋሚ ሰራተኞችን ፋብሪካው ይዟል፡፡ ከቴክኒክ ሙያ የሰለጠኑ ፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃን እና ውዛደሮችን ያካተተ ሲሆን  1000 9ሺህ ብር በወር ይከፈላቸዋል፡፡
ዙራሙሪ ፡- የገበያ ትስስሩ እንዲሁም የመንግስት ድጋፍ  ምን ይመስላል  ?
አቶ ይስማው፡- የመብራት መቆራረጥ ችግር በስፋት በመኖሩ ምክንያት ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ባለመቻሉ እንጂ እስከ አሁን  የገበያ ችግር የለብኝም፡፡ መንግስት በየወሩ 3ሺህ 250 ኩንታል ስንዴ በየወሩ ድጎማ አድርጎልኝ ስንዴውን ፈጭቼ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ እንዳስረክብ እገዛ አድረጎልኛል፡፡
ዙራሙሪ፡- ፋብሪካው በቶሎ ወደ ስራ በመግባቱ ያገኝኽው ማበረታቻ እና እውቅና  በተመለከተስ ?
አቶ ይስማው፡- በዱቄት ጥራት ፣በኪሎ ጥራት እና በንፅህና የክልሉ ንግድ ቢሮ እውቅና ሰጦኛል፡፡በግብር አከፋፍልና  በኢንዱስትሪው ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ተብየ በየትኛውም /ቤት ቅድሚያ መስተናገድ የምችልበት መታወቂያ ተሰጦኛል፡፡
ዙራሙሪ፡- ስለ ግብር መክፈል ያለህ አመለካክት  ?
አቶ ይስማው:- ግብር በመክፈሌ ሰላም አግኝቻለሁ ፣ያፈራሁት ንብረት ተጠብቆልኛል፣መሰረተ ልማቶች በመስፋፋታቸው ተጠቃሚ ነኝ፡፡ስለሆነም ግብር መክፈል ለራስም ለሀገርም ዕድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡
ዙራሙሪ፡- ወደ እርሻ ስንመለስ  ለምን ያህል ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ? ክፍያችውስ ?
አቶ ይስማው፡- 7 ቋሚ ለጊዜያዊ ደግሞ እስከ 300 ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ከቀን ሰራተኛ 100 ቋሚ ሰራተኛ 10 ሺህ ብር እከፍላለሁ፡፡
ዙራሙሪ፡- ለታላቁ  የህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለህ አስተዋፅኦ በተመለከተ ድጋፍህ ምን ይመስላል ?
አቶ ይስማው ፡- 110 ሺህ ብር ቦንድ ያለወለድ  በእኔ እና በቤተሰቦቼ  ስም ገዝቻለሁ፡፡ በቀጣይም ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፌ ይቀጥላል፡፡
ዙራሙሪ፡- ማህበራዊ ህይዎትህ እና ለማህበረሰቡ እያደረግህ ያለው ድጋፍስ ?
አቶ ይስማው፡- በማህበራዊ ህይዎቴ ከሰዎች ጋር ተስማምቼ የምኖር ሰው ስሆን በሀይማኖታዊ ተቋማት ግንባታ የአቅሜን በማድረግ ላይ እገኛለሁ፡፡ሀብት ንብረት ባፈራሁት እሁዲት ከተማ  የእኔ ድርሻ 50% የሆነው 5 ሚሊዮን ብር ግዙፍ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጓድኞቼን በማስተባበር መገንባት ችያለሁ፡፡ሌላው ከእሁዲት ወደ እርሻው የሚወስደውን 15 . የጠጠር መንገድ አሰርቻለሁ፡፡በእንጅባራ ከተማ በአንድ ቤተክርስቲያን ለአዳራሽ ግንባታ 100 ሺህ ብር አስተዋፅኦ አድርጌያለሁ፡፡ በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ በምጠየቅባቸው ልማቶች ሁሉ በግሌና በእርሻው ስም ድጋፍ በማድረግ ላይ እገኛለሁ፡፡በአሁኑ ሰዓት በፋብሪካው ስም አንድ ማየት የተሳነው የዩኒቨርስቲ  ተማሪ በየወሩ  1000 ብር በመክፈል በማስተማር ላይ ነኝ፡፡
ዙራሙሪ ፡- የጊዜ አጠቃቅምህ ምን ይመስላል ?
አቶ ይስማው፡- ኑሮህን  ለመቀየር አንድ ስራ ብቻ መስራት በቂ አይደለም፡፡እኔ ጊዜን በአግባቡ ነው ምጠቀመው ከፋብሪካውና ከእርሻው  ጎን ለጎን ሰሊጥ ከንግዱ ማህበረሰብ በመሰብሰብ በዓመት እስከ 10 ሺህ ኩንታል ለማዕከላዊ ገበያ አቀርባለሁ፡፡ስለሆነም ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ስኬታማ መሆን ይቻላል፡፡
ዙራሙሪ፡- ያንተን ተሞክሮ ለሌሎች በማስተላለፍ ያለህ ልምድ ?
አቶ ይስማው፡- ለእኔ መሰል ነጋዴዎች  እና ወደ ንግዱ አለም ለሚቀላቀሉ ግልሰቦች እኔ ያለፍኩትን ወጣ ውረድ እንዲያዩ ምቹ ሁኔታዎችን አሳያቸዋለሁ፡፡ በዚህ አከባቢ ተባብሮ የመስራት ልምድ ዝቅተኛ ነው ድር ቢያብር ነውናተረቱ መረዳዳት ካለ ብዙ ባለሀብቶችን ማፍራት እንችላለን ፡፡ ስለዚህ እኔ በመተባበርና በመተጋገዝ አምናለሁ፡፡ የእኔን ፈለግ በመከተልም አሁን ላይ ፋብሪካ  በመገንባት ወደ ምርት ማምረት የገቡ ጓደኞችን ማየት ችያለሁ ፡፡
ዙራሙሪ፡- ስኬታማ ነኝ ማለት ትችላለህ ?ወደ ስኬት የሚያደርሱ ዋና ዋና ነገሮችስ ?
አቶ ይስማው፡- እኔ ስኬታማ ሰው ነኝ ከምንም ተነስቼ አሁን ላይ ጥሩ ህይዎት መኖር ጀምሪያለሁ ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ስኬታማ ለመሆን እምነት፣ ጠንክሮ መስራት እና ትግስት ዋና ዋና መሰረታዊ ነገሮች ናቸው፡፡
ዙራሙሪ፡- ጠቅላላ ካፒታልህ ምን ያህል ደርሷል  ? ሀብት ንብረት ?
አቶ ይስማው፡- /ሳቅ/ ጠቅላላ ካፒታሌ እስከ 30 ሚሊዮን ብር  ይደርሳል፡፡ 1ተሳቢ፣የቤት መኪና፣3 መኖሪያ ቤቶች በእሁዲት ከተማ  1 መኖሪያ ቤት በእንጅባራ እንዲሁም 1 ሆቴል አለኝ፡፡
ዙራሙሪ፡- ለዚህ መድረስህ ድጋፍ ያደረጉልህ ግለሰቦች ካሉ ?
አቶ ይስማው፡- በዚያ በከሰርኩበት ወቅት አቶ በላይነህ ክንዴ የእኔን ታሪክ በማጥናት ህይዎቴን የቀየረኝ የመጀመሪያው ሰው ነው፡፡ያለኝን ትንሽ ገንዘብ ከባንክ ጋር በማግናኜት እና በእምነት እስከ 1 ሚሊዮን ብር በማበደር ስኬታማ እንድሆን አግዞኛል፡፡
ዙራሙሪ፡- የባሌቤትህ ድጋፍስ ምን ይመስላል ?
አቶ ይስማማው፡- ከባለቤቴ ጋር የተገናኝነው በባዶ ነው፡፡ለእኔ እዚህ መድረስ የሷ ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡
ዙራሙሪ፡- ባለቤትሽን እንዴት ታግዥዋለሽ ? እንዴት ትገልጭዋለሽ  ?
ወ/ሮ የተመኝ ታደስ፡- ባለቤቴ ቤተሰቦቹን የሚወድ ፣ጠንካራ ሰው ነው ፣በምችለው ሁሉ አግዘዋ ለሁ፣በፋብሪካው የመቆጣጠር ስራዎች እሰራለሁ፡፡
አቶ ይስማው ከባለቤታቸው ከወ/ የተመኝ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው
ዙራሙሪ፡- በጣም የተደሰትክበት ጊዜ እና የአዘንክበት ቀን ካለ ?አቶ ይስማው፡- በህይዎቴ ሁሌም ደስተኛ ነኝ ነገር ግን በጣም የተደሰትኩበት  ጊዜ እሁዲት ከተማ ቤተክርስቲያኑ ሲመረቅ ሲሆን ያዘንኩበት ጊዜ ደግሞ ምንም ባልነበረኝ ወቅት የእርሻው አባላት መሬት ተከፋፈለን እንረስ ያሉኝ ግዜ ነው፡፡
ዙራሙሪ፡- አቶ ይስማውን ከዚህ በኃላ በምን በምን ስራዎች ተሰማርቶ እንጠብቀው ?
አቶ ይስማው፡- የቀጣይ እቅዴ ያሰበኩት ፓስታና መኮረኒ ፋብሪካዎች በቅርቡ ለመጀመር ተዘጋጅቻለሁ፡፡
ዙራሙሪ፡- ሽልማቶችን በተመለከተ ?
አቶ ይስማው፡- 3 የወርቅ ዋንጫ 2 ሜዳሊያ 15 ያላነሱ የምስክር ወረቀቶች  በተለያዩ ጊዚያት ከተለያዩ ተቋማት እውቅና ተሰጦኛል፡፡

ዙራሙሪ፡- የዕድሜውን ግማሽ በበረሃ በመዝመት ስኬታማ የሆነው አቶ ይስማው እምነት እና ጠንክሮ መስራት ዋና መገለጫዎቹ ናቸው፡፡የዙረሙሪ መፅሔት የዝግጅት ክፍላችንም  የዚህን የልማት አርበኛ የሆነው በብሔረሰብ  አስተዳደራችን ግንባር ቀደም ባለሃብቶቻችን መካከል አንዱ ሲሆን በንግዱ ዓለም ለተሰማሩት ሁሉ  የህይዎት ተሞክረው እንደሚያስተምር  ጥርጥር የለንም ፡፡ስለሆነም መልካሙን ሁሉ እየተመኝንልህ እደግ ተመንደግ  እያልን ዝግጅታችንን በዚህ ጨረስን መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ፡፡