የህዝቦች እኩልነትና ፍትሃዊ
ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ፌዴራላዊ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር - ኢትዮጵያ!!
/የመንግስትን
አቋም የሚተነትን ጽሑፍ/
የአገራችን ብሎም የክልላችን እንዲሁም የብሔ/አስተዳደራችን ህዝቦች ለዘመናት
የቋንቋ፣ የሃይማኖትና የባህል ብዝሃነት በማይቀበል ጸረ-ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ አልፈዋል። ይህም በመሆኑ የኢትዩጵያ
ብሔሮች፣ ሔረሰቦችና ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር በተለያየ መልኩ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ጭቆናው እየበረታ በመምጣቱ
በየአካባቢያቸው እየተደራጁ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገቡ አስገድዷቸዋል። የአገሪቱ ኢኮኖሚም ክፉኛ
እየተጎዳ በመምጣቱ ዜጎች ለድህነትና ኋላቀርነት ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ በኢህዴግ መሪነት የኢትዮጵያ ህዝቦች በከፈሉት መስዋእትነት
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም ጸረ ዴሞክራሲያዊው ስርዓት ከመሰረቱ ተወግዶ አዲስ የታሪክ ምእራፍ ተከፍተ።
ግንቦት 20 ብዝሃነትን ያከበረ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ
መሠረት ጥሏል። ህዝቦች ማንነታቸው ተከብሮ በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለመገንባት የሚያስችል ህገመንግስታዊ
ዋስትናም አግኝተዋል። በግንቦት 20 ድል የተረጋገጠው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት ባስከበረው ህገ መንግስታችን የተመሰረተው
የፌዴራል ስርዓት አገሪቱ ከነበረችበት ድህነትና ኋላቀርነት ተላቃ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የቻለችን አዲሲቷ ኢትዮጵያን
ፈጥሯል። በዲፕሎማሲ ረገድም አገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነቷ እና ተማራጭነቷ ከምንጊዜውም በላይ እየጨመረ መጥቷል።
የብሔረሰብ አሰተዳደራችን ህዝብ ግንቦት 20 በፈጠረው አዲስ ምእራፍ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ድሎች እንዲመዘገቡ እድል ከመፍጠሩም በላይ የህዝቡ የልማት ፍላጎት እያደገ መጥቷል።
የህዝቡ የልማት ፍላጎት እያደገ በመምጣቱም ሞጋች ህብረተሰብ ከመፈጠሩ ባሻገር የዲሞክራሲ ሥርዓት በአገራችን የመገንባት ጉዳይም ሰብአዊና
ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ከማስከበር ባለፈ በአገራችን ፈጣን ልማት የማምጣትና ያለማምጣት፣ የአገሪቱን ዲሞክራሲያዊ አንድነት
የማረጋገጥ ወይም የመበታተን ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ልዩ ጥረት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ የሚሄድ
ዲሞከራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ተችሏል፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱን የሚያረጋግጡ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ማለትም የፌዴራል ሥርዓት፣
ም/ቤቶች፣ የፍትህ ተቋማት፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንባ ጠባቂ ተቋማትና የመሳሰሉት አመለካከቶችን ነፃና ሰፊ በሆነ ደረጃ
የሚያስተናግድበት ነባራዊ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ከማግኘታቸው ባሻገር የግልና
የቡድን መብቶች ተከብረዋል፡፡አዳጊ ፍላጎቶችን ለማሟላት በጥልቅ
በመተደስ ብአዴን፣ኢህአድግ እና መንግስት በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ አቋም ይዘው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ይህን ቁርጠኛ አቋም ወደ
ውጤት በመቀየር በተለይ በፌዴራላዊ ስርዓቱ ላይ መግባባት በመፍጠር የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲ ግንባታና መልካም አስተዳደርን
የማስፈን ተግባር ማስቀጠል የለሰለሰ ጥራት የተደረገ ይገኛል።ስለሆነም የዘንድሮው የግንቦት 20 26ኛ አመት በዓል በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት አጠቃላይ ባህሪያት፣ የዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባታ ሂደት፣ ስኬቶች፤ተግዳሮቶችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ስለዚህ ቀጥተኛ
የህዝብ
ተሳትፎን
ማረጋገጥ
የሕብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ስርዓቱ ባህሪ ቢሆንም በአሁን ወቅት ደግሞ የስርዓቱን ፈተናዎች ለማሸነፍ ከመቸውም ጊዜ በላይ ቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎን የሚያሰፋ ንቅናቄ ማቀጣጠል በእጅጉ አስፈላጊ ሆኗል እየተቀጣጠለም ይገኛል፡፡
በተሃድሶው
ወቅት
መግባባት
ከተደረሰባቸው
ጉዳዮች
አንዱም
የተለዩትን
ችግሮች
በመላው
ህዝብ
ተሳትፎ
በየደረጃው
እየፈቱ
መሄድ
ነውና
26ኛውን
የግንቦት
20 የድል
በዓል
ስናከብር
በጥልቅ
ተሃድሶው
የገባንውን
ቃል
በተግባር
ማዋል ይገባል፡፡
አዊ ብሔ/አስ/ መ/ ኮ/ ዋና መምሪያ
ግንቦት 2ዐዐ9




