Friday, 26 May 2017

የህዝቦች እኩልነትና  ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ፌዴራላዊ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር - ኢትዮጵያ!!
/የመንግስትን አቋም የሚተነትን ጽሑፍ/
የአገራችን ብሎም የክልላችን እንዲሁም የብሔ/አስተዳደራችን ህዝቦች ለዘመናት የቋንቋ፣ የሃይማኖትና የባህል ብዝሃነት በማይቀበል ጸረ-ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ አልፈዋል። ይህም በመሆኑ የኢትዩጵያ ብሔሮች፣ ሔረሰቦችና ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር በተለያየ መልኩ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ጭቆናው እየበረታ በመምጣቱ በየአካባቢያቸው እየተደራጁ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገቡ አስገድዷቸዋል። የአገሪቱ ኢኮኖሚም ክፉኛ እየተጎዳ በመምጣቱ ዜጎች ለድህነትና ኋላቀርነት ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ በኢህዴግ መሪነት የኢትዮጵያ ህዝቦች በከፈሉት መስዋእትነት ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም ጸረ ዴሞክራሲያዊው ስርዓት ከመሰረቱ ተወግዶ አዲስ የታሪክ ምእራፍ ተከፍተ።

ግንቦት 20 ብዝሃነትን ያከበረ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ መሠረት ጥሏል። ህዝቦች ማንነታቸው ተከብሮ በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለመገንባት የሚያስችል ህገመንግስታዊ ዋስትናም አግኝተዋል። በግንቦት 20 ድል የተረጋገጠው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት ባስከበረው ህገ መንግስታችን የተመሰረተው የፌዴራል ስርዓት አገሪቱ ከነበረችበት ድህነትና ኋላቀርነት ተላቃ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የቻለችን አዲሲቷ ኢትዮጵያን ፈጥሯል። በዲፕሎማሲ ረገድም አገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነቷ እና ተማራጭነቷ ከምንጊዜውም በላይ እየጨመረ መጥቷል።
የብሔረሰብ አሰተዳደራችን ህዝብ ግንቦት 20 በፈጠረው አዲስ ምእራፍ  ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና  ፖለቲካዊ ድሎች እንዲመዘገቡ እድል ከመፍጠሩም በላይ የህዝቡ የልማት ፍላጎት  እያደገ መጥቷል።
የህዝቡ የልማት ፍላጎት እያደገ በመምጣቱም ሞጋች  ህብረተሰብ ከመፈጠሩ ባሻገር የዲሞክራሲ ሥርዓት በአገራችን የመገንባት ጉዳይም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ከማስከበር ባለፈ በአገራችን ፈጣን ልማት የማምጣትና ያለማምጣት፣ የአገሪቱን ዲሞክራሲያዊ አንድነት የማረጋገጥ ወይም የመበታተን ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ልዩ ጥረት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ የሚሄድ ዲሞከራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ተችሏል፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱን የሚያረጋግጡ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ማለትም የፌዴራል ሥርዓት፣ ም/ቤቶች፣ የፍትህ ተቋማት፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንባ ጠባቂ ተቋማትና የመሳሰሉት አመለካከቶችን ነፃና ሰፊ በሆነ ደረጃ የሚያስተናግድበት ነባራዊ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ከማግኘታቸው ባሻገር የግልና የቡድን መብቶች ተከብረዋል፡፡አዳጊ ፍላጎቶችን ለማሟላት በጥልቅ በመተደስ ብአዴን፣ኢህአድግ እና መንግስት በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ አቋም ይዘው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ይህን ቁርጠኛ አቋም ወደ ውጤት በመቀየር በተለይ በፌዴራላዊ ስርዓቱ ላይ መግባባት በመፍጠር የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲ ግንባታና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ተግባር ማስቀጠል የለሰለሰ ጥራት የተደረገ ይገኛል።ስለሆነም የዘንድሮው የግንቦት 20 26ኛ አመት በዓል በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት አጠቃላይ ባህሪያት፣ የዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባታ ሂደት፣ ስኬቶችተግዳሮቶችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ስለዚህ ቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎን ማረጋገጥ የሕብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ስርዓቱ ባህሪ ቢሆንም በአሁን ወቅት ደግሞ የስርዓቱን ፈተናዎች ለማሸነፍ ከመቸውም ጊዜ በላይ ቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎን የሚያሰፋ ንቅናቄ ማቀጣጠል በእጅጉ አስፈላጊ ሆኗል እየተቀጣጠለም ይገኛል፡፡ በተሃድሶው ወቅት መግባባት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች አንዱም የተለዩትን ችግሮች በመላው ህዝብ ተሳትፎ በየደረጃው እየፈቱ መሄድ ነውና 26ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓል ስናከብር በጥልቅ ተሃድሶው የገባንውን ቃል በተግባር ማዋል  ይገባል፡፡
አዊ ብሔ/አስ/ መ/ ኮ/ ዋና መምሪያ

ግንቦት 2ዐዐ9
























Wednesday, 17 May 2017



ተዘዋዋሪ   ፈንዱ  ለታለመለት..
መንግስት የኢትዮጵያ ወጣቶች የዕድገት እና የልማት ፖኬጅ ቀርፆ የተዘዋዋሪ ፈንድ በመመደብ ወጣቶችን በጥቃንንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በፌዴራል ደረጃ ለወጣቱ ሥራ እድል ፈጠራ 1ዐሚ ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ተመድቦ ለሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች ድልድል የተጠናቀቀ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማለትም የሥራ አጥ ወጣቶች ምልመላና ምዝገባ፣ ግንዛቤ ፈጠራ እና የማማደራጀት ሥራዎች በአብዛኛው ተጠናቀዋል፡፡
በዚህ የወጣቶች የዕድገትና የልማት ፓኬጅ  በክልላችን በሚገኙ ከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የሚገኙ እና ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች የኢትዮትያ  ዜግነት ያላቸውና ከ18-34 ዕድሜ  ባለው ክልል የሚገኙ ይሆናሉ፡፡
ተዘዋዋሪ ፈንዱ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚተላለፍ ሲሆን ባንኩም ለሥራ ዕድል ፈጠራ ለሚታወቀው ለአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በብድር መልክ ያቀርባል፡፡ አበቁተም በክልላችን በሚገኝበት ከተማ  አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለተደራጁ ወጣቶች ይህን ገንዘብ በብድር ያስተዳድራል፡፡ ይህንን የወጣቶች ተዘዋዋሪ ገንዘብ ለታለመለት አላማ በውጤታማነት ለመጠቀም ግልፅ የአሠራር መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡
ወጣት ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር የሚሰጥበት አሠራር፡-
- በኢንተርፕራይዝ ለመደራጀት የሚመለመለው ወጣት በቀበሌው በአንድ ማዕከል የሥራ አጥ መመዝገቢያ መዝገብ ላይ የተመዘገበ መሆን
- የሚመለመለው ወጣት የአዕምሮ ህመም የሌለበት እንዲሁም የደባል ሱስ ተጠቂ ያልሆነ፣ በመጥፎ ሥነ-ምግባር  የማይታወቅ ፣ የመስራት አቅምና ችሎታ ያለው
- የተመለመሉ ወጣቶች የንግድ ሥራ አመራር /የኢንተርፕረነርሽፕ/ ሥልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በሽርክና ማህበር የተደራጁ እና ቢያንስ 5 አንከሳቃሾች ያላቸው መሆን ይኖርባቸል፡፡
- ወጣቶች ሲደራጁ በፍላጐት ላይ የተመሠረተ ሆኖ በተቻለ መጠን የሚተዋወቁና በአንድ አካባቢ የማኖሩ ቢሆኑ ይመረጣል
- የሚደራጁ ወጣቶች ከዚህ ቀደም ከፋይናንስ ተቋማት የተወሰደና  እና የተበላሸ ውዝፍ እዳ የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢንተርፕራይዞቹ የብድሩ ተጠቃሚ ለመሆን ለሥራውም የሚያስፈልገውን ገንዘብ ቢያንስ 1% ከሚወስዱት የተቋሙ ቅርንጫፍ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሚወስዱት ብድር የአንድነትና የነጠላ ዋስትና መፈረም ይኖርባቸዋል ለብድሩ ውጤታማ ተጠቃሚነት የቤተሰብ ትስስር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በኢንተርፕራይዙ የሚደራጁ ወጣቶች ሲመለመሉ መስፈርቱን ለሚያሟሉ  ሴቶች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
- የሥራ መስኩ ምርጫው ሙሉ በሙሉ በኢንተርፕራይዞቹና በአባሎቻቸው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡

የኢንተርፕራይዞች የሥራ መስክ
- ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ገቢ ሊየስገኙ በሚያስችሉ ማናቸውም አይነት የሥራ መስኮች ሊሠማሩ ቢችሉም በክልላችን ተጨባጭ ሁኔታ እድገት ተኮር የሥራ ዘርፎች እና የተመረጡ የአገልግሎት የሥራ ዘርፎች ይሆናሉ፡፡
-ፍላጐታቸውን ማዕከል አድርገው በመረጡት የሥራ መስክ ላይ አዋጭነት ያለው የሥራ ዕቅድ  (Business plan)  ማዘጋጀተ ይኖርባቸዋል፡፡
                  የብድር መጠን
- ኢንተርፕራይዞች የሚወስዱት የብድር መጠን እንደሚሠማሩበት የሥራ ዘርፍ  እና ደረጃ የሚስያማ ቢሆንም ለአንድ ኢንተርፕራይዝ   ሊፈቀድ የሚችለው ከፍተኛው የብድር መጠን ከብር አንድ ሚሊዮን  (1,000,000) eJsB vsjUE!!
      
            የብድር ወለድ
· ጥቃቅን  ኢንተርፕራይዞች በሚወስዱት ብድር ላይ 8 በመቶ አመታዊ ወለድ ይከፍላሉ
· ጤናማ ባልሆኑ ብድሮች ላይ የተጨማሪ 1.5 በመቶ የቅጣት ወለድ ያስከፍላል፡፡


       የብድር መክፈያ ጊዜ
- የኢንተርፕራይዞቹ የሚወስዱት ብድር የመክፈያ ጊዜ እንደተሠማሩበት የሥራ መስክ እና እንደወሰዱት የብድር መጠን ሊለያይ ይችላል፡፡
- በአብዛኛው በአማካይ የብድር መመለሻ ጊዜው 3 ዓመት የሚጠናቀቅ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በተመረጠ ዘርፍ የብድር ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜው እስከ 5 ዓመት ሊደርስ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ ለኢንተርፕራይዞች ውጤታማ የሚማያደርገውን ተከታታይነት ያለው ድጋፍ በመስጠት የመመለሻ ጊዜው በአግባቡ ማስመለስ ይገባል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የአዊ ብሔ/አስ///ኢን//በሥራ ካሉ /ቤቶች ጋር በመሆን 54 በላይ ሥራ ፈላጊዎችን መዝግቦ የማደራጀት ሥራዎች ተጠናቀዋል፡፡
በፌዴራል የተዘዋዋሪ ፈንድ የብሔረሰብ አስትዳደራችን ድርሻ  160 ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ በታች የወረዳዎች ድርሻ ድልድል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 የተዘዋዋሪፈንድበጀትድልድልበየወረዳደረጃ
ተራ
.
የወረዳውስም
የወጣትብዛት
የብርድርሻ /የወጣትቁጥር
*362,316 ብር/
2ዐዐ9 በጀትዓመትድርሻ
ወንድ
ሴት
ድምር
 1
አዊብሔረሰብአስተዳደርዞን





 2
እንጅባራከተማአስተዳደር”
12,356
12,273
24,629
8,923,48.76
4,461,74.38
 3
ዳንግላከተማአስተዳደር
8,512
11,788
2,3ዐዐ
7,355,14.8
3,677,57.4
 4
ቻግኒ
6,494
8542
15,036
544,778,338
272,389,169
 5
ባንጃ
13,638
16,61
3,239
1,956,73.52
5,478,36.76
 6
ጓጉሳሽኩዳድ
16,92
2,554
37,456
13,57,98.1
6,785,454.5
 7
አንከሻ
35,86
42,337
78,143
28,312,459.19
14,156,229.6
 8
ዚገም
15690
18824
34514
12,504,974.42
6,252,487.21
 9
ጓንጓ
2,349
24373
44,772
16,23,496.15
8,11,748.8
1
ጃዊ
26,519
27,190
55,709
20,184,262.04
10,092,131.02
11
ዳንግላወረዳ
21,361
25,122
46,483
16,841,534.63
8,420,767.32
12
ፋግታለኮማ
26,163
28859
5522
1993535.95
9,967,675.48

ድምር
25,79
236,463
442,253
16,235,337.9
8,117668.95
 DSC_0269DSC_1061











 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 በአዊ ብሔ/አስ/መኮ// መምሪያ

መንግስት ኢንፎርሜሽን የሥራ ሂደት የተዘጋጀ

ሚያዚያ  2009 .

 

· ' 0582271428
· 6 0582270037        * 64
· Fb. page Awi communication
   እንጅባራ