የትምህርት ጥራት መሰናክሎች ለመጭው ሀገር ተረካቢ ትውልድ በሽታ ናቸው!!
ትምህርት የእድገት ሁሉ መሰረት ነው፡፡ምክንያቱም ትምህርት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ እሴቶችን ለማዳበርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ለማጠናከር የአመለካክት ለውጥ ለማምጣት ቁልፍ መሳሪያችን ስለሆነ፡፡ትምህርት የአመለካከትና የአስተሳስብ አድማስን በማስፋት የምርምርና የፈጠራ ችሎታን በማዳበር፣ ለምርትና ምርታማነት መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማፋጠን የሚያስችል ወደር የለሽ ሚና ያለው ነው፡፡
መንግስት ትምሀርት ለልማት ፣ለሰላም፣ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር ችግር
መፍቻ ቁልፍ ሚና የሚጫወት
መሆኑን በውል በመገንዘብ እና
ለዘርፉ እድገት ልዩ ትኩረት በመስጠት
በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎች ሰብዕናው በተሟላ መንገድ በእውቀት፣በክህሎት፣በመልካም ስነ-ምግባር እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ
እሴቶችንና መርሆችን የተገነባ ዜጋ ማፍራት የሚያስችል የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ቀርፆ በስራ ላይ አውሏል፡፡ከፍተኛ መዋለ
ንዋይ መድቦ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመዘርጋት እና የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
በብሔረሰብ አስተዳዳሩ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከዚህ
በፊት በየዓመቱ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በክልሉና በአገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ስለሆነም
በ2010 በጀት ዓመት 10ኛ እና 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ
ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች 10ኛ ክፍል በ34 ትምህርት ቤቶች ወንድ
9,221 ሴት 11,185 በድምሩ 20,406 ሲሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ20 ትምህርት ቤቶች ወንድ 2,726
ሴት 2,650 በድምሩ 376 ተማሪዎች አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ይሁን እንጂ የትምህርት ጥራት መሰናክሎች በርካታ ሲሆኑ እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር የተለዩት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የትምህርት ግብዓቶች በወቅቱ አለመሟላት
2. የትምህርት ጥራት መርሃ ግብሮችን በአግባቡ በትምህርት ቤቶች ላይ አለመተግበር
3. ተማሪዎችን በተገቢው መንገድ አለመመዘን
4. የመብራት መቆራረጥና ከእነጭራሹ አለመኖር
5. የኩረጃ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ መዳበር
6. የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ደረጃውን
ሳያሟሉ መከፈት
7.የትምህርት አመራሮች የአመለካከት ችግር መኖርና የመሳሰሉት የትምህርት ጥራት መሳናክሎች ናቸው፡፡
1.የትምህርት ግብዓቶች በወቅቱ አለመሟላት
የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ ግብዓት ወሳኝ ነው፡፡ይኸውም አዳዲስ ትምህርት ቤቶችና በገጠር አከባቢ የሚገነቡ ት/ቤቶች
የፕላዝማና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን አለመሟላት፣የቤተ-መጽሐፈፍት ቁሳቁሶችና የተማሪዎች ማስተማሪያ መጽሐፍ በወቅቱ
አለመመደብ፣የሰው ሀይል እጥረትና በሙያው የሰለጠኑ መምህራን በሰለጠኑበት ሙያ አለመመደብ ችግር ናቸው፡፡
2. የትምህርት ጥራት መርሃ ግብሮችን በአግባቡ በትምህርት ቤቶች
ላይ አለመተግበር
የትምህር ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆች ስድስት መርሀ ግብሮች ያሉት ሲሆን እነዚህ መርሀ-ግብሮች በትክክልና በተገቢው መንገድ
በት/ቤቶች በመተግበር የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ መርሀ-ግብሮችን በትምህርት ቤቶች ላይ
በተገቢው መንገድ አለመተግበር የሚያመጣው ችግር ነው፡፡ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ መርሃ ግብሮች ስርዓተ-ትምህርት
መርሃ ግብር፣መምህራን ልማት መርሀ-ግብር፣ስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መርሃ ግብር ፣ኢንፎርሜሽን ኮሚኒከሽን ቴክኖሎጂ መርሀ
ግብር፣የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀ ግብር እና የትምህርት ቤት አመራርና አስተዳደር መርሀ ግብር ናቸው፡፡
3.
ተማሪዎችን በተገቢው
መንገድ አለመመዘን
ከትምህርት ጥራት እንቅፋቶች አንዱ ተማሪዎችን በተገቢውና በሚያውቁት ልክ አለመመዘን ሲሆን ይህም መምህራን ለተማሪዎች የተከታታይ የምዘና ውጤት በግምትና በግዴልሽነት እንዲሁም ሀላፊነት በሚሰማው መንገድ ውጤት ያለመስጠት ችግር ነው፡፡
4.የመብራት መቆራረጥና ከእነ ጭራሹ አለመኖር
መንግስት የትምህርት ሽፋኑን ተደራሽና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ተግባራዊ ለማድረግ በከተማና በገጠር ወረዳዎች በርካታ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤቶች ተገንብተዋል፡፡
በገጠር አካባቢ በሚገነቡት ት/ቤቶች የመብራትና የሌሎች መሰረተ ልማቶች ተደራሽነት ባለመኖሩ ተማሪዎች የፕላዝማና ሌሎች የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ወስደው ተወዳዳሪ አለመሆን መሰረታዊ ችግር ነው፡፡
5 የኩረጃ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ መዳበር
ተማሪዎች ጊዜዊ ተስፋ በማድረግና በራስ አለመተማመን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በቂ የትምህርት ዝግጅት ያላደረጉ ተማሪዎች ከጎበዝና በራስ የሚተማመኑ ተማሪዎች ላይ በመኮረጅ ፈተና እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡
በተለይም ጥቂት ሃላፊነት የማይሰማቸዉ የትምህርት አመራሮች የ10ኛ እና የ12ኛ
ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላይ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው በመኮራረጅ ከፍተኛ ውጤት እንዲያመጡ ድጋፍ ይደረጋሉ፡፡ የ10ኛ እና
የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያመጣው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ት/ቤት ተሸላሚ ስለሚሆን፡፡ከዚህ በተጨማሪ በራሳቸው
የማይተማመኑ አንዳንድ ተማሪዎች ፈተናን ለመኮረጅ እንዲመቻቸው የጎበዝ ተማሪዎች ስም ጋር ለማመሳሰል በፍርድቤት ስም የመቀየር በስፋት የሚታይ በሽታ ነው፡፡ይህ የኩረጃ ባህልና የስም መቀየር
እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር የከፋ ቸህግር እየሆነ መጥቷል፡፡
6.የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ሳያሟሉ መከፈት
መንግስት የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ ሲባል በየአካባቢው የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች የመመዘኛ ደረጃ ሳያሟሉ
በየገጠር ባሉ ወረዳዎችና መሰረተ ልማት ሳያሟሉ መከፈት አንዱ የትምህርት ጥራት ችግር ነው፡፡
7.የትምህርት አመራሮች የአመለካከት ችግር መኖር
የትምህርት አመራሮች የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ በመሆን የትምህርት ተቋማትን
አለመምራት፡፡
በተለይም 10ኛ እና 12ኛ
ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች መሰረት ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም በግምት ውጤት በመስጠትና በመኮራረጅ ተመሳሳይ
ውጤት እንዲያመጡ በማድርግ የመጭውን ሀገር ተረካቢ ትውልድ በትምህርት የታነፀ በስነምግባሩ የተስተካከለ እንዲሆን አለማድረግ፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ትምህርት ዋና መምሪያ የትምህርት ጥራት መሰናክሎች ለማስወገድ በ2010 በጀት ዓመት እያደረገ የለው
የቅድመ ዝግጅት ዕርምጃዎች
መምሪያው የትምህርት ጥራት መሰናክሎች ለመቅረፍ
ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ለ10ኛ እና ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን በራስ የመተማመን መንፈስ
ኑሮቸው ተረጋግተው ፈተና እንዲወስዱ የሚከተሉትን ስልቶች ቀይሷል፡፡
1. የወላጆች፣የተማሪዎችና የትምህርት ባለድርሻ አካላትን መድረክ በመፍጠር የግንዛቤ ትምህርት መስጠት መቻሉ
2. በ36 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣በ157 ሱፐርቫይዘሮችና በ501 ፈተኝ መምህራንና
ለትምህርት አመራሮች ኦረንቴሽን በመስጠት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ከማድረግ ባሻገር ጎበዝ/በራሳቸው የሚተማመኑ
ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲፈተኑ የብቻቸውን ተለየተው እንዲፈተኑ ማድረጉ
3. በራሳቸው የማይተማመኑ ተማሪዎች ከጎበዝ ተማሪዎች የስም ማመሳሰል እንዳይደረግ ከዳኞች
ጋር ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ማድረጉ
4. በአጠቃላይ ተማሪዎች በራስ በመተማመን ተረጋግተውና ተገቢውን ዝግጅት አድርገው ፈተና
እንዲወስዱ ከባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት ላይ መድረስ መቻል፡፡
