Tuesday, 25 April 2017



ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 6ኛ ዓመት በዓል ጋር በማስተሳሰር ሲካሄድ የነበረው የአዊ ብሔረሰብ የባህል ፌሲቲባል ተጠናቀቀ፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ያዘጋጀው ይህ የባህል ፌሲቲባል ሲዘጋጅ ለሁለተኛ ሲሆን ነው፡፡ በፌስቲባል ንግግር ያደረጉት የብሔ/አስ/ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ባይነሳኝ ካሳሁን የብሔረሰቡ ማንነት መግለጫ የሆነው ባቱ ባህል፣ቋንቋ ታሪክና ቅርስ በመጪ ባህል እየተበረዘ በመሆኑ ከእታዊ መጤ ባህሎች የመታደግ ሁላችንም ኃላፊነት አለብን፡፡
የዚህ ፌስቲባል መካሄድ ዋና ዓላማውም የየአካባቢያቸውን ባህል ይዘው የመጣ ተሳታፊዎች እርስ በእርስ ልምዳቸውን የሚለዋወጡበትና ተተኪ ከያንያንን ለማደራጀትም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
ከፌስቲባሉ ተሳታፊዎች መካከል አበበ ወርቁ እንደተናገረው በየወረዳው ያሉ አማተር ከያንያንን እርስ በእርስ ልምድ እንድንለዋወጥ ከማስቻሉ ባሻገር በብሔረሰብ አስተዳደሩ ብዙ ያልተነሱ ባህሎች ያሉ ስለሆነ አጉልቶ ለማሳየትና ጥንታዊ ባህላችንን ጠብቀን ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ኃላፊነት እንደሚጠበቅብን ያሳየነው  ብሏል፡፡
በፌስቲባሉ 12 የባህል ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በተሰጣቸው መስፈርቶች በመወዳደር የአዊ ባህልና ኪነ ጥበባት ቡድን አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡ ይህ ቡድን በክልል ደረጃ በሚደረገው የፌስቲባል ውድድር ብሄረሰብ አስተዳደሩ ወክሎ የሚሳተፍ እንዲሆንም ተናግረዋል፡፡




v  ህገ-ወጥ የእንቁላል ነጋዴዎች በሚፈጥሩት ውዥንብር የምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል ዋጋ መቀነስ ለዶሮ አርቢዎች ትልቅ ችግር እንደሆነ ተገለፀ፡፡
v  በአዊ ብሔ/አስተዳደር በምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል ዋጋ መቀነስ በዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ሊያሳጣ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
በአዊ ብሔ/አስተዳደር እንስሳት ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ መከተ እንዳሉት ሀገራችን በእንስሳት ሃብት ልማት በዓለም 5ኛ በአፍሪካ 1ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ የኢኮኖሚ ዘርፍ በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እስከ ቀበሌ ድረስ የሰው ሃይል መድቦ እንቅስቃሴ እየተደረገ   በት ያለ ዘርፍ ነው፡፡ የዶሮ ሀብት ልማት በብሔረሰብ አስዳደራችን በሰፊው እየተሰራ ይገኛል፡፡ ወጣቶችን በማደራጀት የ1 ቀን ጫጩት በመስጠት እንዲያሳድጉ እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከ52ሽ በላይ ደሮዎችን ላርሶ አደሩ ተሰራጭቷል፡፡ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ለ 1 ሴት 25 ደሮዎችን በመስጠት ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡ ጥሩ ስራ እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች በሚፈጥሩት ውዥንብር የተሻሻሉ ዶሮዎች እንቁላል ዋጋ መውረድ ትልቅ ችግር መሆኑን አውስተዋል፡፡ አረሶ አደሮች የተሻሻሉ ደሮዎችን የማርባት ፍላጎት እንዲቀንስ አድርገዋል፡፡ ያሏቸውንም ዶሮዎች በርካሽ እየሸጡ ይገኛሉ፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ከንግድ ገበያ ልማት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ሥራ ይሠራል ብለዋል፡፡ በህ/ሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ለመስራት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የእንስሳት በሽታ ግኝትና ቁጥጥር ባለሙያ ዶ/ር ምንውየለት አያና በሀገራችን የተለያዩ የዶሮ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ የሚሰጡትም የስጋ እና የእንቁላል ምርት ጣዕም ይለያያል ብለዋል፡፡ ጎጃም ላይ ያለው መቀንጨር ጋር ተያይዞ የተከሰተው በሽታ ይስተካከላል ተብሎ የሚታሰበው የፕሮቲን ምግቦችን በመጠቀም ነው፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግ የምርጥ ዘር ዶሮዎች መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዶሮዎች እንቁላላቸው ለምግብነት ብቻ የሚያገለግል ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት እንቁላሉ ችግር እንዳለበት የሚወሩ አላስፈላጊ ጥቅም ለማግኘት የተደረገ ስልት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡን ነጋዴዎች መካከል አቶ ጌትነት ፈንቴ እና አቶ ምስጋናው ወንድም እንደተናገሩት ህብረተሰቡ በአብዛኛው የሀበሻ ዶሮዎችን እንቁላል ስለሚፈልግ የምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል ዋጋ እንዲቀንስ ተጽዕኖ ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም የሀበሻ ዶሮ እንቁላል በ2 ብር ሲሸጥ የምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል በ1 ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዶሮ እርባታ ተጠቃሚዎች መካከል አቶ በለጠ አያሌው እና  አቶ አዱኛ ሰማኸኝ እንደገለጹት የደሮ እርባታ ስራ ማንኛውም ሰው ሊሰራው የሚችል ትልቅ የገቢ ምንጭ ነው፡፡ ዶሮ እንድናረባ ያነሳሳን የስራው ውጤታማ መሆን ነው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምንገዛው የዶሮ መኖ እና የእንቁላል ዋጋ ስላልተመጣጠነ በስራቸው ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ መንግስትም በአፋጣኝ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል ሲል የአዊ ብሔ/አስ/መ/ኮ/ጉ/ዋና መምሪያ ዘግቧል፡፡



ዘመናዊ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስረዓትን አስተማማኝ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ቅንጅታዊ የአሰራር ዘዴን መከተል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
የአዊ ብሔ/አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ዞናዊ ኮንፈረንስ በእንጅባራ ከተማ ለ2 ቀናት አካሂዷል፡፡
ኮንፈረንሱ በብሄ/አስተዳደሩ በመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ስረዓት ላይ ያሉ ችግሮችንና መፍትሔዎች ዙሪያ ከአጋር አካላት፣ከአመራሮችና ከባለሙያዎች ጋር ሠፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የአዊ ብሔ/አስተዳደር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርጋ ወሌ እንደገለጹት የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በብቃት መምራትና ማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ ግዴታ ነው፡፡ አቶ ይርጋ አክለውም በዘርፉ የመሬት ወረራ፣የህፃናት፣የአቅመ ደካሞችም በስፋት ይስተዋላል፡፡ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና መሬትን በማዘመን የመሬትን አስተዳደርና አጠቃቀም ስረዓትን አስተማማኝና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ከአጋር አካላት ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ የአሰራር ዘዴን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡ በብሄ/አስተዳደሩ 96.5 የመጀመሪያ ደረጃ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠቱን የጠቆሙት ኃላፊው 1ኛ ደረጃ ደብተር መሰጠትም 18 የደረሰ ሲሆን መረጃውን ወደ ኮምፒዩተር የማስገባት ስራዎችም መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ 948 ሄ/ር ያለአግባብ የተመሰረተ መሬት ወደ መሬት ባንክ መመለሱን የገለጹት አቶ ይርጋ ለ7ሽ 712 ወጣቶች 821.25 ሄ/ር መሬት መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡፡
የብሄ/አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየን ብረሃን በበኩላቸው በገጠርና በከተማ ህገ-ወጥነት በመስፋፋቱ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሁነዋል፡፡ ችግሮችን ለማሰወገድ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ከምንጩ ማስወገድ አልተቻለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይ ህገ-ወጥ ቤቶች የተገነቡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ህ/ሰቡን በሚያሳትፍ በመስረተ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይ መከላከል ይገባል ብለዋል፡፡










ልማታዊ መንግስት ለቋንቋዎች ዕድገት!
ልማታዊ መንግስት ለዜጎች ካጎናፀፋቸው መብቶች አንዱና መሰረታዊ ጉዳይ የዜጎችን ሠባዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ማክበርና ማስከበር ነው፡፡ ይህም ሲባል ዜጎች የራሳቸውን ቋንቋና ባህል በማሳደግ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ፣ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ እንዲሁም የራሳቸውን ባህል እንዲያሳድጉ ማድረግ ነው፡፡
ውድ አንባቢያን በዚህ ዓምድ ልማታዊ መንግስት ዜጎች አፍ መፍቻ ቋንቋቸውን እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው የወሰደቸው የህግ ማዕቀፉ የሰጣቸውን መብቶች ለማሳየት እንሞክራለን፡፡
የኢ... ህገ - መንግስት ካጎናፀፏቸው ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ህገ - መንግስታዊ መብቶች አንዱ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመናገር መብት ነው፡፡ እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋው የመናገር፣ የመፃፍ፣ ቋንቋውን የማሳደግ፣ባህሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመግለጽ መብት አለው፡፡ ሆኖም ባለፉት ዘመናት ዜጎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመናገር መብታቸው ተነፍጓቸው በማንነታቸው እንዲሸማቀቁ፣ በቋንቋቸውና በባህላዊ አኗኗር ዘይቤአቸው እንዳይኖሩ፣ ትውፊታቸውንና ወጋቸውን እንዳያለሙ በጨቋኝና አፋኝ ስርዓቶች ጫና ይደረግ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ይሁን እንጅ በዜጎች መራር ትግል እነዚያ የግፍ ዘመናት ድል ተደርገው ዛሬ ላይ ሁነን ስንቃኘው የአገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች በህገ -መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን መብት በመጠቀም 46 ቋንቋዎች የፅሁፍና የትምህርት ቋንቋ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ ከዚህም መካከል 17 ቋንቋዎች በፊደል እስክሪፕት እና 29 በላቲን እስክሪፕት የሚጠቀሙ ናቸው፡፡
የኢ... የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት አንፃር የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋዎች ስነ ቃሎች ትውፊቶች፣ኪነ-ጥበባዊ እውቀቶች ለአገልግሎት እንዲውሉ፣ የቋንቋና የጋራ ባህላዊ እሴቶች እንዲበለፅጉ፣መጤንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲወገዱ፣ የህዝቦች አመለካከት ለማህበራዊ እድገት ለምተውና በልጽገው ለሀገራዊ ልማት እንዲውሉ ማድረግ  ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡ ተግባራቱ እውን እንዲሆኑ በህብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በማጥናት፣ በልማትና በማስተዋወቅ እንዲሁም የአገሪቷን መልካም ገጽታ በመገንባት ዘላቂ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲሰጡ ተልዕኮ በመያዝ ያላለሳለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አገራችን ብዙሃነት ተቀብላ በእኩልነት እያስተናገደች ያለች ሀገር እንደመሆኗ ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት/ ዩኔስኮ/ ጋር ካደረገቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች አንዱ በቋንቋ ብዙሃነት ላይ የተደቀነውን ስጋት አብሮ በመስራት ለመቀነስ እንዲሁም የቋንቋ ልማት በሀገሪቱ እንዲረጋገጥ ከህብረተሰቡ ጋር ግንዛቤ የሚፈጥሩ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ የኢ... ህገ - መንግስት በምዕራፍ 1 በአንቀጽ 5 /1-3/ ላይ ማናቸውም የኢትዮጲያ ቋንቋዎች በእኩልነት የመንግስት እውቅና ይኖራቸዋል፡፡ አማርኛ የፌዴራሉ መንግስት የስራ ቋንቋ ይሆናል፤ የፌዴሬሽኑ /ቤት አባሎች የየራሳቸውን የስራ ቋንቋ በህግ ይወሰናሉይላል፡፡ በአንቀጽ 39/2/ ደግሞማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ በቋንቋው የመናገር፣የመፃፍ፣ ቋንቋቸውን የማሳደግ እና ባህሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመግለጽ መብት አለው ይላሉ፡፡
የባህል ፖሊሲያችን ለቋንቋዎቻችን ልማት የሠጠው ትኩረት፣
የኢ... መንግስት የባህል ፖሊሲ በተመሳሳይ መልኩ ከህግ መንግስታዊ ጽንስ ሀሳቦች መነሻ ተቀርጾ 1990 / ፀድቆ ወደ ስራ ተገብቶ እየተሰራበት የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የአለም አቀፍ እና የአገራችን የባህል ኢንዱስትሪዎች እድገት ተጨባጭ ሁኔታዎችን በመገንዘብ እንዲከለስ ተደርጓል፡፡ የባህል ፖሊሲው ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለጋራና ለተናጥል እድገታቸው መሰረት የሆኑ የጋራ የባህል እሴቶቻቸውን ማጎልበት እንዲችሉ ዋስትና ሰጥቷል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ቋንቋዎች እና ስነ - ቃሎች የልማት አቅጣጫ በርካታ ነገሮችን ያውሳል፡፡ በሰነዱ በተለያዩ አንቀጾች እንደተመለከተው በመላው አገሪቱ የሚገኙ ቋንቋዎች እና ቀበልኛዎች በስፍራና በደረጃ ተለይተው እንዲመዘገቡ ይደርጋል፤የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦች፣ ስነ - ቃሎች በሚነገሩበት ስፍራ ታሪካዊና ባህላዊ እሴታቸው የተጠበቀበት ሳይንሳዊ ምዝገባ ይደረግላቸዋል ይላል፡፡ እንዲሁም የሀገሪቱን ቋንቋዎች ስርጭት የሚያመለክት የቋንቋ ካርታ ይዘጋጃል፡፡ ፊደል ለሌላቸው ቋንቋዎች የተናጋሪው ህብረተሰብ ስነ ልቦናና አመለካከት የተገነዘበበት የፊደል ቀረፃ በማከናወን አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ ፊደል ያሏቸው ቋንቋዎች ያለባቸውን ችግር ለመፍታት በአፃፃፍ ስርአት ጥናት ላይ የተመረኮዘ ማሻሻያ ይደረግላቸዋል፤ በሀገሪቱ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦች ቋንቋዎች መዛግብተ ቃላትን፣ አውደ ጥበቦችንና የሰዋሰው መፃህፍትን በማዘጋጀት የህዝቦች  ስነ ጽሁፋዊ ባህል የሚዳብርበት ሁኔታ ያመቻቻል ይላል፡፡
 




 

ብሔር ብሔረሰቦች በዓል በተለያየ ዝግጅት ሲከበር
የአፍ መፍቻ ቋንቋ ስንል አንድ ሰው በህፃንነቱ ከሁሉም በፊት የሚማረው እና አካባቢውን የሚረዳበት፣ የሚገልጽበትና የሚግባባበት የመጀመሪያ ቋንቋ ነው፡፡
በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ጥቅሞች በጥቂቱ፤
· በህፃናት የቋንቋ እና የትምህርት እድገት ወሳኝ የሆነ
አወንታዊ ውጤት ያመጣል፣ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሲማሩ የሚማሩት ቋንቋውን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ትምህርቶች ጽንስ ሀሳቦችንና ክህሎቶችን የሚያሳድጉበት ነው፣የህፃናት የአፍ መፍቻ ቋንቋ እድገት ለተጨማሪ ቋንቋዎች እድገት አመልካች ነው፣ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ያዳርሳል፣የህሊና ልማት በማምጣት ሙሉ ስብእናው የተገነባ በማንነቱ የሚኮራ ትውልድ ለመቅረጽ ያግዛል፣አካባቢውን የሚገነዘብ ሁኔታዎችንና ክስተቶችን በቀላሉ የሚረዳ ለለውጥ ዝግጁ የሆነ ዜጋን ማፍራት ይቻላል፡፡ ለእውቀት ሽግግር ንቁ እና ለፈጠራ ችሎታ ብቁ የሆነን ዜጋን ያበረክታል፡፡
ሀገር በቀል እውቀቶችን በማሳደግ በባህላዊ ምርቶች ተጠቃሚነትን ያጠናክራል፡፡
በቋንቋው ተናጋሪ ህብረተሰብ አስተዳደርም ሆነ በተለያዩ ሙያዎች በስራ ቋንቋነት የማገልገል እድል ይፈጥራል፡፡ ይህን መሰረት በማድረግም የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የአዊኛ እንደ አፍ መፍቻ በማስተማር ደረጃ ያለበትን ሁኔታ በተማሪዎች፣በመምህራን እና በትምህርት ቤቶች በሚከተለው ሠንጠረዥ ለማሳየት እንሞክራለን፡፡
      
                           ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ


መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ

ዓመተ ምህረት
የተቋማት ብዛት
የመምህራን ብዛት
የተማሪ ብዛት
ሴክሽን
ጥምርታዎች
አዊኛ አንድ 1 የትም/ዓ/የሚሰጥ ተቋማት




1987











1988











1989
5
10

10
191
72
263
8
1፡26
1፡33

1990
65
109
11
120
5948
2605
8553
123
1፡71
1፡70

1991
70
138
29
167
11875
6741
18616
197
1፡111
1፡94

1992
72
189
106
295
16317
10388
26705
295
1፡91
1፡91

1993
72
199
133
332
20197
13494
33691
387
1፡101
1፡











1994
73
236
157
393
20387
13590
33977
390
1፡86
1፡

1995
76
402
224
626
21056
14437
35493
443
1፡57
1፡

1996
80
327
216
543
23094
17548
40642
541
1፡75
1፡
10
1997
96
526
358
884
30352
25461
55813
797
1፡63
1፡
60
1998
111
553
485
1038
35085
30620
65705
1009
1፡63
1፡
80
1999
135
767
477
1244
36795
33643
70438
1118
1፡57
1፡
102
2000
140
822
574
1396
43222
40146
83368
1420
1፡60
1፡
160
2001
167
1206
769
1975
46700
44429
91129
1593
1፡47
1፡

2002
189
1074
859
1933
45702
45257
90959
1652
1፡48
1፡
187
2003
210
1234
896
2130
50003
50559
100562
2014
1፡48
1፡

2004
227
1417
989
2406
46739
48293
95032
2121
1፡40
1፡45

2005
231
1703
1014
2717
47622
50858
98480
2029
1፡39
1፡49

2006
242
1746
1127
2873
52029
53572
105601
2243
1፡37
1፡47

2007
254
1770
1241
3011
55657
54732
110389
2405
1፡37
1፡45

2008
265
1826
1288
3114
59463
58907
118370
2600
1፡38
1፡46

ምንጭ አዊ ብሔ/አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

















ከላይ በሰንጠረዥ እንደተመለከተው በሁሉም ዘርፍ አሃዛዊ መረጃው እያደገ የመጣ ቢሆን ቋንቋውን ለማሳደግ እና ከነበረበት የአመለካከት ችግር ከማውጣት ግን መሰረታዊ ችግር ያለበት መሆኑን ልንገናዘብ ችለናል፡፡ስለሆነም ውድ አንባቢያን ልማታዊ መንግስታችን ለቋንቋዎች እድገት የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በተለይም በከተማ ህብረተሰብ አካባቢ ለቋንቋው ያለውን የአመለካከት ችግር እንዲሁም በአመራሩ፣በወላጁ፣በተማሪዎች እና በአጠቃላይ የማህበረሰብ ክፍል ላይ እየታየ ያለውን የትኩረት ማነስ እና የአመለካከት ችግር ለመቅረፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል፡፡