Tuesday, 25 April 2017




ዘመናዊ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስረዓትን አስተማማኝ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ቅንጅታዊ የአሰራር ዘዴን መከተል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
የአዊ ብሔ/አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ዞናዊ ኮንፈረንስ በእንጅባራ ከተማ ለ2 ቀናት አካሂዷል፡፡
ኮንፈረንሱ በብሄ/አስተዳደሩ በመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ስረዓት ላይ ያሉ ችግሮችንና መፍትሔዎች ዙሪያ ከአጋር አካላት፣ከአመራሮችና ከባለሙያዎች ጋር ሠፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የአዊ ብሔ/አስተዳደር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርጋ ወሌ እንደገለጹት የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በብቃት መምራትና ማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ ግዴታ ነው፡፡ አቶ ይርጋ አክለውም በዘርፉ የመሬት ወረራ፣የህፃናት፣የአቅመ ደካሞችም በስፋት ይስተዋላል፡፡ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና መሬትን በማዘመን የመሬትን አስተዳደርና አጠቃቀም ስረዓትን አስተማማኝና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ከአጋር አካላት ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ የአሰራር ዘዴን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡ በብሄ/አስተዳደሩ 96.5 የመጀመሪያ ደረጃ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠቱን የጠቆሙት ኃላፊው 1ኛ ደረጃ ደብተር መሰጠትም 18 የደረሰ ሲሆን መረጃውን ወደ ኮምፒዩተር የማስገባት ስራዎችም መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ 948 ሄ/ር ያለአግባብ የተመሰረተ መሬት ወደ መሬት ባንክ መመለሱን የገለጹት አቶ ይርጋ ለ7ሽ 712 ወጣቶች 821.25 ሄ/ር መሬት መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡፡
የብሄ/አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየን ብረሃን በበኩላቸው በገጠርና በከተማ ህገ-ወጥነት በመስፋፋቱ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሁነዋል፡፡ ችግሮችን ለማሰወገድ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ከምንጩ ማስወገድ አልተቻለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይ ህገ-ወጥ ቤቶች የተገነቡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ህ/ሰቡን በሚያሳትፍ በመስረተ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይ መከላከል ይገባል ብለዋል፡፡








No comments:

Post a Comment