ተዘዋዋሪ ፈንዱ ለታለመለት…..
መንግስት የኢትዮጵያ ወጣቶች የዕድገት እና የልማት ፖኬጅ ቀርፆ የተዘዋዋሪ ፈንድ በመመደብ ወጣቶችን በጥቃንንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በፌዴራል ደረጃ ለወጣቱ ሥራ እድል ፈጠራ 1ዐሚ ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ተመድቦ ለሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች ድልድል የተጠናቀቀ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማለትም የሥራ አጥ ወጣቶች ምልመላና ምዝገባ፣ ግንዛቤ ፈጠራ እና የማማደራጀት ሥራዎች በአብዛኛው ተጠናቀዋል፡፡
በዚህ የወጣቶች
የዕድገትና የልማት ፓኬጅ በክልላችን በሚገኙ ከተማ አስተዳደሮች፣
ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የሚገኙ እና ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች የኢትዮትያ ዜግነት ያላቸውና ከ18-34 ዕድሜ ባለው ክልል የሚገኙ ይሆናሉ፡፡
ተዘዋዋሪ ፈንዱ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚተላለፍ ሲሆን ባንኩም ለሥራ ዕድል ፈጠራ ለሚታወቀው ለአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በብድር መልክ ያቀርባል፡፡ አበቁተም በክልላችን በሚገኝበት ከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለተደራጁ ወጣቶች ይህን ገንዘብ በብድር ያስተዳድራል፡፡ ይህንን የወጣቶች ተዘዋዋሪ ገንዘብ ለታለመለት አላማ በውጤታማነት ለመጠቀም ግልፅ የአሠራር መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡
ለወጣት ጥቃቅን እና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች ብድር የሚሰጥበት አሠራር፡-
- በኢንተርፕራይዝ ለመደራጀት የሚመለመለው ወጣት በቀበሌው በአንድ ማዕከል የሥራ አጥ መመዝገቢያ መዝገብ ላይ የተመዘገበ መሆን
- የሚመለመለው ወጣት የአዕምሮ ህመም የሌለበት እንዲሁም የደባል ሱስ ተጠቂ ያልሆነ፣
በመጥፎ ሥነ-ምግባር የማይታወቅ ፣ የመስራት አቅምና ችሎታ ያለው
- የተመለመሉ ወጣቶች የንግድ ሥራ አመራር /የኢንተርፕረነርሽፕ/ ሥልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በሽርክና ማህበር የተደራጁ እና ቢያንስ 5 አንከሳቃሾች ያላቸው መሆን ይኖርባቸል፡፡
- ወጣቶች ሲደራጁ በፍላጐት ላይ የተመሠረተ ሆኖ በተቻለ መጠን የሚተዋወቁና በአንድ አካባቢ የማኖሩ ቢሆኑ ይመረጣል
- የሚደራጁ ወጣቶች ከዚህ ቀደም ከፋይናንስ ተቋማት የተወሰደና እና የተበላሸ ውዝፍ እዳ የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢንተርፕራይዞቹ የብድሩ ተጠቃሚ ለመሆን ለሥራውም የሚያስፈልገውን ገንዘብ ቢያንስ 1ዐ% ከሚወስዱት የተቋሙ ቅርንጫፍ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሚወስዱት ብድር የአንድነትና የነጠላ ዋስትና መፈረም ይኖርባቸዋል ለብድሩ ውጤታማ ተጠቃሚነት የቤተሰብ ትስስር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በኢንተርፕራይዙ የሚደራጁ ወጣቶች ሲመለመሉ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሴቶች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
- የሥራ መስኩ ምርጫው ሙሉ በሙሉ በኢንተርፕራይዞቹና በአባሎቻቸው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡
የኢንተርፕራይዞች የሥራ መስክ
- ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ገቢ ሊየስገኙ በሚያስችሉ ማናቸውም አይነት የሥራ መስኮች ሊሠማሩ ቢችሉም በክልላችን ተጨባጭ ሁኔታ እድገት ተኮር የሥራ ዘርፎች እና የተመረጡ የአገልግሎት የሥራ ዘርፎች ይሆናሉ፡፡
-ፍላጐታቸውን ማዕከል አድርገው በመረጡት የሥራ መስክ ላይ አዋጭነት ያለው የሥራ ዕቅድ (Business plan) ማዘጋጀተ ይኖርባቸዋል፡፡
የብድር መጠን
- ኢንተርፕራይዞች የሚወስዱት የብድር መጠን እንደሚሠማሩበት የሥራ ዘርፍ እና ደረጃ የሚስያማ ቢሆንም ለአንድ ኢንተርፕራይዝ ሊፈቀድ የሚችለው ከፍተኛው የብድር መጠን ከብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) eJsB vsjUE!!
የብድር ወለድ
· ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በሚወስዱት ብድር ላይ የ8 በመቶ አመታዊ ወለድ ይከፍላሉ
· ጤናማ ባልሆኑ ብድሮች ላይ የተጨማሪ 1.5 በመቶ የቅጣት ወለድ ያስከፍላል፡፡
የብድር መክፈያ ጊዜ
- የኢንተርፕራይዞቹ የሚወስዱት ብድር የመክፈያ ጊዜ እንደተሠማሩበት የሥራ መስክ እና እንደወሰዱት የብድር መጠን ሊለያይ ይችላል፡፡
- በአብዛኛው በአማካይ የብድር መመለሻ ጊዜው በ3 ዓመት የሚጠናቀቅ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በተመረጠ ዘርፍ የብድር ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜው እስከ 5 ዓመት ሊደርስ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ ለኢንተርፕራይዞች ውጤታማ የሚማያደርገውን ተከታታይነት ያለው ድጋፍ በመስጠት የመመለሻ ጊዜው በአግባቡ ማስመለስ ይገባል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የአዊ ብሔ/አስ/ቴ/ሙ/ኢን/ል/በሥራ ካሉ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን ከ54ሺ በላይ ሥራ ፈላጊዎችን መዝግቦ የማደራጀት ሥራዎች ተጠናቀዋል፡፡
በፌዴራል የተዘዋዋሪ ፈንድ የብሔረሰብ አስትዳደራችን ድርሻ 160 ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ በታች የወረዳዎች ድርሻ ድልድል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የተዘዋዋሪፈንድበጀትድልድልበየወረዳደረጃ

|
ተራ
ቁ.
|
የወረዳውስም
|
የወጣትብዛት
|
የብርድርሻ /የወጣትቁጥር
*362,316
ብር/
|
የ2ዐዐ9 በጀትዓመትድርሻ
|
||
|
ወንድ
|
ሴት
|
ድምር
|
||||
|
1
|
አዊብሔረሰብአስተዳደርዞን
|
|
|
|
|
|
|
2
|
እንጅባራከተማአስተዳደር”
|
12,356
|
12,273
|
24,629
|
8,923,48ዐ.76
|
4,461,74ዐ.38
|
|
3
|
ዳንግላከተማአስተዳደር
|
8,512
|
11,788
|
2ዐ,3ዐዐ
|
7,355,ዐ14.8ዐ
|
3,677,5ዐ7.4ዐ
|
|
4
|
ቻግኒ
|
6,494
|
8542
|
15,036
|
544,778,338
|
272,389,169
|
|
5
|
ባንጃ
|
13,638
|
16,6ዐ1
|
3ዐ,239
|
1ዐ,956,ዐ73.52
|
5,478,ዐ36.76
|
|
6
|
ጓጉሳሽኩዳድ
|
16,9ዐ2
|
2ዐ,554
|
37,456
|
13,57ዐ,9ዐ8.1ዐ
|
6,785,454.ዐ5
|
|
7
|
አንከሻ
|
35,8ዐ6
|
42,337
|
78,143
|
28,312,459.19
|
14,156,229.6ዐ
|
|
8
|
ዚገም
|
15690
|
18824
|
34514
|
12,504,974.42
|
6,252,487.21
|
|
9
|
ጓንጓ
|
2ዐ,349
|
24373
|
44,772
|
16,2ዐ3,496.15
|
8,1ዐ1,748.ዐ8
|
|
1ዐ
|
ጃዊ
|
26,519
|
27,190
|
55,709
|
20,184,262.04
|
10,092,131.02
|
|
11
|
ዳንግላወረዳ
|
21,361
|
25,122
|
46,483
|
16,841,534.63
|
8,420,767.32
|
|
12
|
ፋግታለኮማ
|
26,163
|
28859
|
55ዐ22
|
1993535ዐ.95
|
9,967,675.48
|
|
|
ድምር
|
2ዐ5,79ዐ
|
236,463
|
442,253
|
16ዐ,235,337.9
|
8ዐ,117668.95
|




በአዊ ብሔ/አስ/መኮ/ጉ/ዋና መምሪያ
መንግስት ኢንፎርሜሽን የሥራ ሂደት የተዘጋጀ
ሚያዚያ 2009 ዓ.ም
· ' 0582271428
· 6 0582270037 * 64
· Fb. page Awi
communication
እንጅባራ
No comments:
Post a Comment