v ህገ-ወጥ የእንቁላል ነጋዴዎች በሚፈጥሩት ውዥንብር የምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል
ዋጋ መቀነስ ለዶሮ አርቢዎች ትልቅ ችግር እንደሆነ ተገለፀ፡፡
v በአዊ ብሔ/አስተዳደር በምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል ዋጋ መቀነስ በዘርፉ
የሚገኘውን ጥቅም ሊያሳጣ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
በአዊ ብሔ/አስተዳደር እንስሳት ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት
ኃላፊ አቶ ነጋ መከተ እንዳሉት ሀገራችን በእንስሳት ሃብት ልማት በዓለም 5ኛ በአፍሪካ 1ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ የኢኮኖሚ ዘርፍ
በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እስከ ቀበሌ ድረስ የሰው ሃይል መድቦ እንቅስቃሴ እየተደረገ በት ያለ ዘርፍ ነው፡፡ የዶሮ ሀብት ልማት በብሔረሰብ አስዳደራችን በሰፊው
እየተሰራ ይገኛል፡፡ ወጣቶችን በማደራጀት የ1 ቀን ጫጩት በመስጠት እንዲያሳድጉ እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከ52ሽ በላይ
ደሮዎችን ላርሶ አደሩ ተሰራጭቷል፡፡ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ለ 1 ሴት 25 ደሮዎችን በመስጠት ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡
ጥሩ ስራ እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች በሚፈጥሩት ውዥንብር የተሻሻሉ ዶሮዎች እንቁላል ዋጋ መውረድ ትልቅ ችግር መሆኑን
አውስተዋል፡፡ አረሶ አደሮች የተሻሻሉ ደሮዎችን የማርባት ፍላጎት እንዲቀንስ አድርገዋል፡፡ ያሏቸውንም ዶሮዎች በርካሽ እየሸጡ ይገኛሉ፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ ከንግድ ገበያ ልማት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ሥራ ይሠራል ብለዋል፡፡ በህ/ሰቡ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ለመስራት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የእንስሳት በሽታ ግኝትና ቁጥጥር
ባለሙያ ዶ/ር ምንውየለት አያና በሀገራችን የተለያዩ የዶሮ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ የሚሰጡትም የስጋ እና የእንቁላል ምርት ጣዕም ይለያያል
ብለዋል፡፡ ጎጃም ላይ ያለው መቀንጨር ጋር ተያይዞ የተከሰተው በሽታ ይስተካከላል ተብሎ የሚታሰበው የፕሮቲን ምግቦችን በመጠቀም
ነው፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግ የምርጥ ዘር ዶሮዎች መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዶሮዎች እንቁላላቸው ለምግብነት ብቻ የሚያገለግል
ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት እንቁላሉ ችግር እንዳለበት የሚወሩ አላስፈላጊ ጥቅም ለማግኘት የተደረገ ስልት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡን ነጋዴዎች መካከል አቶ ጌትነት
ፈንቴ እና አቶ ምስጋናው ወንድም እንደተናገሩት ህብረተሰቡ በአብዛኛው የሀበሻ ዶሮዎችን እንቁላል ስለሚፈልግ የምርጥ ዘር ዶሮዎች
እንቁላል ዋጋ እንዲቀንስ ተጽዕኖ ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም የሀበሻ ዶሮ እንቁላል በ2 ብር ሲሸጥ የምርጥ ዘር ዶሮዎች እንቁላል በ1
ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዶሮ እርባታ ተጠቃሚዎች መካከል አቶ በለጠ አያሌው እና አቶ አዱኛ ሰማኸኝ እንደገለጹት የደሮ እርባታ ስራ ማንኛውም ሰው ሊሰራው
የሚችል ትልቅ የገቢ ምንጭ ነው፡፡ ዶሮ እንድናረባ ያነሳሳን የስራው ውጤታማ መሆን ነው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምንገዛው የዶሮ
መኖ እና የእንቁላል ዋጋ ስላልተመጣጠነ በስራቸው ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ መንግስትም በአፋጣኝ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች
ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል ሲል የአዊ ብሔ/አስ/መ/ኮ/ጉ/ዋና መምሪያ ዘግቧል፡፡
No comments:
Post a Comment