Monday, 24 April 2017

                       ሰፖርት በአዊ
ስፖርት የሰውን ልጅ አካላዊና አዕምሮአዊ ብቃት የሚያጎለብት እና የገቢ ምንዛሬ ነው፡፡ ስፖርት ሀገርን ከሀገር ጋር አንድነትን፣ፍቅርን እና መተሳሰብን እንዲኖር የሚያደርግ የስሜት ቋንቋ የሚፈጥር ማህበራዊ ዘርፍ ነው፡፡ ሀገራችንም በዓለም በሚደረጉ ስፖርት ውድድሮች ተሳታፊ ናት፡፡ በተለያዩ ዘርፎች በማሸነፍ ስሟን ማስጠራት ተችሏል፡፡ በተለይም በአትሌቲክስ /ሩጫ/ ውድድር በስመጥር /ጀግና አትሌቶች/ ሰንደቅ አላማዋን ከፍ አድርጎ ማውለብለብ ተችሏል፡፡ የሀገራችን ስምና ዝና በዓለም አደባባይ የሚያስጠሩ ስመ ጥር ስፖርተኞች መገኛ ከኛው አካባቢ በሚደረግ ትናንሽ የስፖርት እንቅስቃሴዎች የተነሱ ናቸው፡፡ ብሔ/አስተዳደራችንን ወክለው ሲጫወቱና ሲሮጡ የነበሩ ስፖርተኞች ዛሬ የሀገራችን ስም ማስጠራት ችለዋል፡፡ አሁንም በቀጣይ የሀገራቸውን ስም የሚያስጠብቁ ብቁና ተወዳዳሪ ስፖርተኞች ለማፍራት በየደረጃው የተለያዩ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡






ስፖርተኞች በልምምድ ላይ
የአዊ ብሄ/አስተዳደር የተተኪ ስፖርተኞች የማፍራት ስራ በሰፊው እየተሰራ ይገኛል፡፡ ስፖርት የህዝብ ሀብት እንደመሆኑ መጠን ሊያድግና ሊጎለብት የሚችለው በመላ ህዝብ ዙሪያ በሚደረግ ተሳትፎ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ከዚህም በመነሳት በየደረጃው በሚገኝ ከቀበሌ ጀምሮ ኮሚቴዎችን በማደራጀት ስፖርት ህዝባዊ መሰረት ኖሮት እንዲመራና የተሻለ ለውጥ እንዲያመጣ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ብዙ ስራ ተሰርቷል፡፡  ከሁሉም በላይ በወረዳና ከተማ አስተዳደርዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ በማወያየት ክለቦችን የበጋና የክረምት ቡድኖችን በስማቸው በመያዝ ቀላል የማይባል ድጋፍ እያደርጉ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ውጤታማ የሆኑት አትሌቶችን ለክልሉ በማዋጣት የአማራ ክልል ላስመዘገበው ውጤት ብሄረሰብአስተዳደሩ የበኩሉን ድርሻ ማበረከት ችሏል፡፡
2ተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከተቀመጠው ዋና ዋና ግቦች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ማስፋፋት፣ማልማት እና ህጋዊነታቸውን በማረጋገጥ ህብረተሰቡ እንደየ ፍላጎቱና ችሎታው እንዲቀሳቀሱባቸው ማድረግ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ቢያንስ አንድ የማዘውተሪያ ቦታ እንዲኖር ዕቅድ የተሰጠን ቢሆንም አብዛኛው ከተማ አስተዳደር ዕቅዳቸውን ከግማሽ በላይ አሳክተዋል፡፡ ዳንግላ ከተማ አስተዳዳርና አንከሻ ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ እና ባንጃ በመካከለኛ ያሳኩ ናቸው፡፡ በዝቅተኛ የቀረቡ ደግሞ ጃዊ፣ዚገም፣ዳንግላ ወረዳና ፋግታ ለኮማ ናቸው፡፡
ጨዋታዎች፣የባህል ስፖርት ውድድር እና በመሳሰሉት ስፖርቱን ዘርፍ ለማጠናከር በብሄረሰብ አስተዳደር በሚገኙ  ወረዳዎች እና ከተ/አስተዳደሮች ውድድር ይዘጋጃል፡፡
የአካባቢያችን ስፖርት መሰረቱ ሰፊ እንዲሆንና አስፈላጊውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ በክረምት 2 ወራት በበጋ ደግሞ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ለተከታታይ 7 ወራት ስልጠና ይሰጣል፡፡አቋራጭ ውድድር የወረዳና ከተ/አስተዳደር የመላው አዊ በክረምትና በበጋ የመሰረታዊ ስልጠና ከሚያገኙ ታዳጊ ወጣቶች መካከል የተሻለ ክህሎትና ለየት ያለ ፍላጎት ያላቸውን የስፖርት ቤተሰቦች በማሰባሰብ ለተከታታይ 4 ዓመት ስልጠና ይሠጣል፡፡ አገር የፕሮጀክት ስልጠና እራሱን የቻለ አካሄድ አለው፡፡ የህይወት ታሪክ ይሞላል፤ በአሰልጣኝነት የሚመረጡ የተሻለ ብቃት  ያላቸውን አሰልጣኞች ከመሆኑም በላይ የሚጠቀሙበት የስልጠና ቁሳቁስ ከበጋና ከክረምት ስልጠናዎች ማደግ አለበት፡፡ ከነዚህም የፕሮጀክት ስልጠና ታዳጊ ወጣቶች በኢትዩጵያ ሴቶች ፕሪሜሪሊግ ክለብ ኢትዩጵያ ቡና፣እቴጌ እግር ኳስ ክለብ፣በቅድስት ማሪያም በኢትዩጵያ ወጣቶች አካዳሚ እና በተለያዩ የሥልጠና ማዕከላትና ክለቦች 13 ታዳጊ ወጣቶች ከብሔ/አስተዳደራችን ተመርጠው በስፖርቱ የሥራዕድልተፈጥሮላቸዋል፡፡






የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን
የአዊ ልማት ማህበር የአትሌቲክስ ክለብ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር እረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ሲሆን በዓመት ውስጥ 350,000,00 ብር በላይ ልምድ በማድረግ በአገራችን የሚገኙ ትላልቅ ክለቦችና የስፖርት አካዳሚዎች በመግባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡
2008 / ጀምሮ አዊ ልማት በአገር አቋራጭና በመላው ጨዋታ እራሱን ችሎ መወዳደር ቢችልም ተገቢውን ውጤት ለማስመዝገብ አልተቻለም፡፡ የአካባቢው አትሌቶች የተሻለ ክፍያ ወዳለበት ክለቦች መሄድ እንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡ ሌላው በብሔረሰብ አስተዳደራችን የሚገኘው የአዊ እምፕልታቅ እግር ኳስ ክለብ ነው፡፡ክለቡ 25 ስፖርተኞችና 1 አሰልጣኝ በመቅጠር በብሔ/አስተዳደር፣በወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እየተደረገለት ይገኛል፡፡ በዚህ ክለብ ጥሩ እና ተወዳዳሪ ስፖርተኞች ያሉበት ቢሆንም የተቻለውን ያህል ርቀት ሄዶ ከመወዳደር ላይ ክፍተት ስላለ ውጤት ማስመዝገብ አልተቻለም፡፡ በዚህም የፋይናንስ እጥረት እንቅፋት እንደ ምክንያት ይቀርባል፡፡
 





በአጠቃላይ የብሔረሰብ አስተዳደራችን በተለያዩ የስፖርት ዘርፍ እንቅስቃሴ ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ ያለበት ሁኔታ ነው፡፡
 ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያ ሁሉም ህብረተሰብ በተቻለው መጠን እየተንቀሳቀሰ ቢገኝም አጥጋቢ ነው ማለት ስለማይችል በየዘርፉ ትልቅ ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡
የሀገራችን ስም የሚያስጠሩና ሰንደቅ ዓላማዋን የሚያውለበልብ  ትውልድ ለመፍጠር ስለ ስፖርት ሰፊ ግንዛቤ ህብረተሰቡ እንዲኖረው ሰፊ እንቅስቃሴ መደረግ ይኖርበታል፡፡                                                                          

No comments:

Post a Comment